እነሆ፥ ቅዱሳኑን እንኳን አያምናቸውም፥ ሰማያትም በፊቱ ንጹሐን አይደሉም።
እነሆ፤ እግዚአብሔር በቅዱሳኑ እንኳ አይታመንም፤ ሰማያትም በርሱ ፊት ንጹሓን አይደሉም።
እግዚአብሔር በመላእክቱ ላይ እምነት የለውም፤ ሰማያት እንኳ በእርሱ ፊት ንጹሓን አይደሉም፤
እነሆ፥ በቅዱሳኑ እንኳ አይታመንም፤ ሰማይም በፊቱ ንጹሕ አይደለም።
እነሆ፥ በቅዱሳኑ ስንኳ አይታመንም፥ ሰማያትም በፊቱ ንጹሐን አይደሉም።
ከፍ ከፍ ባሉት ላይ ለሚፈርደው እግዚአብሔር ሰው እውቀትን ሊያስተም ይችላልን?
እነሆ፥ ጨረቃ እንኳ ብሩህ ካልሆነች፥ ከዋክብትም በፊቱ ንጹሐን ካልሆኑ።
እነሆ፥ በአገልጋዮቹ እንኳን አይተማመንም፥ በመላእክቱንም ላይ ስሕተት ያገኛል፥
“አሁንም ተጣራ፥ የሚመልስልህ አለን? ከቅዱሳንስ ወደማናቸው ትዞራለህ?