ኢዮብ 14:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለዘለዓለም ታሸንፈዋለህ፥ እርሱም ያልፋል፥ ፊቱን ትለውጣለህ፥ እርሱንም ትሰድደዋለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንድ ጊዜ ፈጽመህ ትበረታለህ፤ እርሱም ያልፋል፤ ገጽታውን ትቀይራለህ፤ ትሸኘዋለህም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኀይልህ ለዘለዓለም በእርሱ ላይ ይበረታል፤ እርሱም እንዳልነበረ ይሆናል፤ መልኩንም ለውጠህ ከፊትህ ታስወግደዋለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለዘለዓለም ታስወግደዋለህ፥ እርሱም ያልፋል፤ ፊትህን ትመልስበታለህ፥ እርሱንም ትሰድደዋለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለዘላለም ታሸንፈዋለህ፥ እርሱም ያልፋል፥ ፊቱን ትለውጣለህ፥ እርሱንም ትሰድደዋለህ። |
ከሩቅም ሆነው ዓይናቸውን ባነሡ ጊዜ አላወቁትም፤ ድምፃቸውንም አሰምተው አለቀሱ፥ እያንዳንዳቸውም መጐናጸፊያቸውን ቀደዱ፥ ወደ ላይም ወደ ራሳቸው ላይ ትቢያ ነሰነሱ።
መንፈስን ለማገድ በመንፈስ ላይ ሥልጣን ያለው ሰው የለም፥ በሞቱም ቀን ላይ ሥልጣን የለውም፥ በጦርነትም ውስጥ መሰናበቻ የለም፥ ክፋትም ሠሪውን አያድነውም።
ሔት። ፊታቸው ከጥቀርሻ ይልቅ ጠቁሮአል፥ በመንገድም አልታወቁም፥ ቁርበታቸው ወደ አጥንታቸው ተጣብቆአል፥ ደርቆአል፥ እንደ እንጨት ሆኖአል።