ኢዮብ 13:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሥጋዬን በጥርሴ እይዛለሁ፥ ሕይወቴንም በእጄ አኖራለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሥጋዬን በጥርሴ፣ ሕይወቴንም በእጄ ለምን እይዛለሁ? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ጥርሴን ነክሼ ስጨነቅ የምኖረው ለምንድን ነው? ሕይወቴም በእጄ ላይ ነች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሥጋዬን በጥርሴ እይዛለሁ፤ ሕይወቴንም በእጄ አጥብቄ አኖራታለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሥጋዬን በጥርሴ እይዛለሁ፥ ሕይወቴንም በእጄ አኖራለሁ። |
አስጨናቂዎችሽንም ሥጋቸውን አስበላቸዋለሁ፥ እንደ ጣፋጭም ወይን ጠጅ ደማቸውን ጠጥተው ይሠክራሉ፤ ሥጋ ለባሹም ሁሉ እኔ ጌታ መድኃኒትሽና ታዳጊሽ፥ የያዕቆብ ኃያል እንደሆንሁ ያውቃል።
ምናሴ ኤፍሬምን፤ ኤፍሬም ምናሴን ይበላል፤ በይሁዳም ላይ በአንድነት ይነሣሉ፤ ይህም ሁሉ ሆኖ፤ ቁጣው ገና አልበረደም፤ እጁም እንደ ተዘረጋ ነው።
እኔም እንደማትረዱኝ በተረዳሁ ጊዜ በሕይወቴ ቈርጬ አሞናውያንን ለመውጋት ተሻገርሁ፤ ጌታም ድሉን ሰጠኝ፤ ታዲያ ዛሬ እኔን ለመውጋት የመጣችሁት ለምንድን ነው?”
ዳዊት ፍልስጥኤማዊውን የገደለው በገዛ ሕይወቱ ቆርጦ ነው። ጌታ ለመላው እስራኤል ታላቅ ድልን አቀዳጀ፤ አንተም አይተህ ደስ አለህ። ታዲያ እርሱን በከንቱ በመግደል ዳዊትን በመሰለ ንጹሕ ሰው ላይ ለምን በደል ትፈጽማለህ?”
ሴቲቱም ወደ ሳኦል መጥታ ሲንቀጠቀጥ ስላየችው እንዲህ አለችው፦ “እኔ አገልጋይህ የአንተን ቃል ሰምቼ ሕይወቴን እስከ ማሳለፍ ደርሼ አለሁ፤ ያልከኝንም ነገር አዳመጥኩ፤