ኢዮብ 13:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክብሩስ አያስፈራችሁምን? ግርማውስ አይወድቅባችሁምን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ግርማው አያስደነግጣችሁምን? ክብሩስ አያስፈራችሁምን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክብሩ አያስፈራችሁምን? ግርማውስ አያስደነግጣችሁምን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጥንቱን ኀይሉ አያስፈራችሁምን? ግርማስ ከእርሱ ዘንድ አይወድቅባችሁምን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ክብሩስ አያስፈራችሁምን? ግርማውስ አይወድቅባችሁምን? |
ሕዝብህ እስኪያልፍ ድረስ፥ ጌታ ሆይ የገዛኸው ሕዝብ እስኪያልፍ ድረስ፥ በኃይልህ ታላቅነት፥ ፍርሃትና ድንጋጤ ወደቀባቸው፥ እንደ ድንጋይ ቀጥ አሉ።
ጌታ ግን እውነተኛ አምላክ ነው፤ እርሱም ሕያው አምላክና የዘለዓለም ንጉሥ ነው፤ ከቁጣው የተነሣ ምድር ትንቀጠቀጣለች፤ አሕዛብም መዓቱን መቋቋም አይችሉም።
በውኑ እኔን አትፈሩምን? ይላል ጌታ፤ ከፊቴስ አትደነግጡምን? አልፎት እንዳይሻገር አሸዋን በዘለዓለም ትእዛዝ ለባሕር ድንበር አድርጌአለሁ፤ ሞገዱም ቢናወጥ አያሸንፍም፥ ቢጮኽም አያልፈውም።