የነገሥታትንም እስራት ይፈታል፥ ወገባቸውንም በመታጠቂያ ያስራቸዋል።
ነገሥታትን ድግ ያስፈታል፤ ገመድም በወገባቸው ያስራል።
እርሱ ነገሥታትን ከዙፋናቸው ያወርዳል፤ ሽርጥ የታጠቁ እስረኞችም ያደርጋቸዋል።
ነገሥታትንም በዙፋን ያስቀምጣቸዋል፤ ወገባቸውንም በኀይል መታጠቂያ ያስታጥቃቸዋል።
በአለቆች ላይ ንቀትን ያፈስሳል፥ የብርቱዎችንም መታጠቂያ ያላላል።
የፈረሰውን ለራሳቸው ከሚሠሩት ከምድር ነገሥታትና አማካሪዎች ጋር፥
የቀስቴን አውታር አላልቶብኛል፥ አዋርዶኝማል፥ እነርሱም በፊቴ ልጓማቸውን ፈትተዋል።
አቤቱ፥ እኔ አገልጋይህ ነኝ፥ አገልጋይህ፥ የሴት አገልጋይህም ልጅ ነኝ፤ ሰንሰለቴን ሰበርህ።
በመካከላቸው ደካማና ስንኩል አይገኝም፤ የሚያንቀላፋና የሚተኛ አይኖርም፤ የወገባቸው መቀነት አይላላም፤ የጫማቸውም ማሰሪያ አይበጠስም።
የዮሐንስ ልብስ ከግመል ጠጉር የተሠራ ነበር፥ በወገቡም ጠፍር ይታጠቅ ነበር፤ ምግቡም አንበጣና የበረሓ ማር ነበር።
በልብሱና በጭኑም ላይ “የነገሥታት ንጉሥና የጌታዎች ጌታ” የሚል ስም ተጽፎአል።