በዚህ ጊዜ፥ “ከአቤሴሎም ጋር ካሤሩት መካከል አንዱ አኪጦፌል ነው” ብለው ለዳዊት ነገሩት። ዳዊትም፥ “ጌታ ሆይ! እባክህን የአኪጦፌልን ምክር ወደ ከንቱነት ለውጠው” ሲል ጸለየ።
ኢዮብ 12:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አማካሪዎችንም እራቁታቸውን ይሰዳቸዋል፥ ፈራጆችንም ሞኝ ያደርጋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አማካሪዎችን ከጥበባቸው ያራቍታል፤ ፈራጆችንም ማስተዋል ይነሣል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ አማካሪዎችን ጥበብ ይነሣቸዋል፤ የሕዝብ መሪዎችንም ሞኞች ያደርጋቸዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መካሮችንም እንዲማረኩ ያደርጋቸዋል፤ የምድር ፈራጆችንም አላዋቆች ያደርጋቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መካሮችንም እንደ ዘረፋ ይወስዳቸዋል፥ ፈራጆችንም ያሳብዳል። |
በዚህ ጊዜ፥ “ከአቤሴሎም ጋር ካሤሩት መካከል አንዱ አኪጦፌል ነው” ብለው ለዳዊት ነገሩት። ዳዊትም፥ “ጌታ ሆይ! እባክህን የአኪጦፌልን ምክር ወደ ከንቱነት ለውጠው” ሲል ጸለየ።
አቤሴሎምና የእስራኤል ሰዎች ሁሉም “ከአኪጦፌል ምክር ይልቅ የአርካዊው የሑሻይ ምክር ይሻላል” አሉ፤ ጌታ በአቤሴሎም ላይ ጥፋት ለማምጣት፥ ጌታ መልካም የነበረው የአኪጦፌል ምክር ተቀባይነት እንዲያጣ አድርጎአል።
አኪጦፌልም ምክሩን እንዳልተከተሉት ባየ ጊዜ፥ አህያውን ጭኖ ቤቱ ወደሚገኝበት ወደ መኖሪያ ከተማው ሄደ፤ ቤቱንም አስተካክሎ በገዛ እጁ ታነቀ፤ ከሞተ በኋላ በአባቱም መቃብር ተቀበረ።
ስለዚህ፥ እነሆ፥ ድንቅ ነገርን በዚህ ሕዝብ መካከል፥ አስደማሚ ነገርን ተአምራትንም እንደገና አደርጋለሁ፤ የጥበበኞችም ጥበብ ትጠፋለች፥ የአስተዋዮችም ማስተዋል ትሰወራለች።