“በውኑ እግዚአብሔር ከሰው ጋር በምድር ላይ ይኖራልን? እነሆ፥ ሰማይ ከሰማያትም በላይ ያለ ሰማይ አንተን መያዝ አይችልም፤ ይልቁንስ እኔ የሠራሁት ቤት እንዴት ያንስ ይሆን?
ኢዮብ 11:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሰማይ ይልቅ ከፍ ይላል፥ ምን ልታደርግ ትችላለህ? ከሲኦልም ይልቅ ይጠልቃል፥ ምን ልታውቅ ትችላለህ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሰማይ ይልቅ ከፍ ይላል፤ ምን ልታደርግ ትችላለህ? ከሲኦልም ይጠልቃል፤ ምን ልታውቅ ትችላለህ? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእርሱ ታላቅነት ከሰማይ በላይ ነው፤ አንተ ምን ልታደርግ ትችላለህ? ጥልቀቱም ከሲኦልም በታች ነው፤ አንተ ምን ታውቃለህ? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰማይ ከፍ ያለ ነው፤ ምን ልታደርግ ትችላለህ? ከሲኦልም ይልቅ የጠለቁ ነገሮች አሉ፤ ምን ታውቃለህ? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሰማይ ይልቅ ከፍ ይላል፥ ምን ልታደርግ ትችላለህ? ከሲኦልም ይልቅ ይጠልቃል፥ ምን ልታውቅ ትችላለህ? |
“በውኑ እግዚአብሔር ከሰው ጋር በምድር ላይ ይኖራልን? እነሆ፥ ሰማይ ከሰማያትም በላይ ያለ ሰማይ አንተን መያዝ አይችልም፤ ይልቁንስ እኔ የሠራሁት ቤት እንዴት ያንስ ይሆን?
ወደ ሰማይ የወጣ የወረደስ ማን ነው? ነፋስንስ በእጁ የጨበጠ ማን ነው? ውኃንስ በልብሱ የቋጠረ ማን ነው? የምድርን ዳርቻ ሁሉ ያጸና ማን ነው? ይህን ታውቅ እንደሆንህ፥ ስሙ ማን የልጁስ ስም ማን ነው?