እንዳልነበረ በሆንሁ፥ ከማኅፀንም ወደ መቃብር በወሰዱኝ።
ምነው ባልተፈጠርሁ! ወይም ከማሕፀን ቀጥታ ወደ መቃብር በወረድሁ!
ሳልፈጠር በቀረሁ፥ ከማሕፀንም በቀጥታ ወደ መቃብር ብወሰድ ኖሮ በተሻለኝ ነበር።
እንዳልነበረስ ለምን አልሆንሁም? ከማኅፀንም ወደ መቃብር ለምን አልወረድሁም?
“ስለምን ከማኅፀን አወጣኸኝ? ዐይን ሳያየኝ ምነው በሞትሁ።
የሕይወቴ ቀኖች ጥቂት አይደሉምን?
በጨለማው አልተደመሰስኩም፥ ነገር ግን ድቅድቁ ጨለማ ፊቴን ሸፈነ።”
በማኅፀን ሳለሁ ስለምን አልሞትሁም? ከሆድስ በወጣሁ ጊዜ ስለምን ፈጥኜ አልጠፋሁም?
ወይም እንደ ተደበቀበ ጭንጋፍ፥ ብርሃንም እንዳላዩ ሕፃናት በሆንሁ ነበር።
እንደሚፈስስ ውኃ ይጥፉ፥ ቀስትን ሲገትሩ ፍላጻው ይጣመም።
እናቴ መቃብር እንድትሆነኝ ማኅፀንዋም ዘወትር ይዞኝ እንዲቆይ በማኅፀን ውስጥ አልገደለኝምና።