ኢዮብ 10:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምስክሮችህን ታድስብኛለህ፥ ቁጣህንም ታበዛብኛለህ፥ ጭፍራ በጭፍራ ላይ ትጨምርብኛለህ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም አዳዲስ ምስክሮችን ታመጣብኛለህ፤ ቍጣህንም በላዬ ትጨምራለህ፤ ሰራዊትህም ተከታትሎ ይመጣብኛል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእኔ ላይ የሚመሰክሩ ሰዎች ዘወትር ታገኛለህ፤ በእኔ ላይ የምታሳየው ቊጣ እያደገ ይሄዳል፤ እኔን ለማጥቃት ዘወትር አዳዲስ ዕቅዶችን እንደ ሠራዊት ታሰልፍብኛለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳግመኛም ከጥንት ጀምሮ ትመረምረኛለህ፤ ታላቅ መቅሠፍትን አመጣህብኝ። ፈተናዎችንም ላክህብኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምስክሮችህን ታድስብኛለህ፥ ቍጣህንም ታበዛብኛለህ፥ ጭፍራ በጭፍራ ላይ ትጨምርብኛለህ። |
ሞዓብ ከብላቴንነቱ ጀምሮ ተረጋግቷል፥ በአምቡላውም ላይ ዐርፎአል፥ ከዕቃም ወደ ዕቃ አልተንቈረቈረም፥ ወደ ምርኮም አልሄደም፤ ስለዚህ ቃናው በእርሱ ውስጥ ቀርቶአል፥ መዓዛውም አልተለወጠም።
በዚያም ዘመን ኢየሩሳሌምን በመብራት እፈትሻለሁ፤ በአተላቸውም ላይ የሚረጉትን፥ በልባቸውም፦ “ጌታ መልካምም ክፉም አያደርግም” የሚሉትን ሰዎች እቀጣለሁ።
በሙላት ወጣሁ፥ ጌታም ባዶዬን መለሰኝ፤ ጌታ በእኔ ላይ ሰቆቃን ሲያደርስ፥ ሁሉን የሚችል አምላክ አስጨንቆኛልና፥ ናዖሚ ብላችሁ ለምን ትጠሩኛላችሁ?” አለቻቸው።