ኤርምያስ 9:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፥ አቀልጣቸዋለሁ እፈትናቸዋለሁም፤ ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ክፋት ከዚህ ሌላ የማደርገው ምንድነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ እንደ ብረት አነጥራቸዋለሁ፤ እፈትናቸዋለሁም፤ ስለ ሕዝቤ ኀጢአት፣ ከዚህ የተለየ ምን ማድረግ እችላለሁ? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም የተነሣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቤን ለማጥራት እንደ ብረት እፈትናቸዋለሁ፤ ሕዝቤ ክፉ ነገር ስለ ፈጸሙ ይህን ከማድረግ በቀር ሌላ ምን አደርጋቸዋለሁ? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ አቀልጣቸዋለሁ፤ እፈትናቸውማለሁ፤ ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ክፋት እንደዚሁ አደርጋለሁና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ አቀልጣቸዋለሁ እፈትናቸውማለሁ፥ ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ክፋት ከዚህ ሌላ የማደርገው ምንድር ነው? |
በእውነት ኤፍሬም የተወደደ ልጄ ነውን? ወይስ ደስ የምሰኝበት ሕፃን ነውን? በእርሱ ላይ በተናገርሁ ቍጥር አሁንም ድረስ በትክክል አስታውሰዋለሁ፤ ስለዚህ አንጀቴ ታወከችለት ርኅራኄም እራራለታለሁ፥ ይላል ጌታ።
በኢየሩሳሌም መንገድ እየተመላለሳችሁ ሩጡ፥ ተመልከቱም፥ እወቁም፥ በአደባባይዋም ፈልጉ፤ ፍርድን የሚያደርገውን እውነትንም የሚሻውን ሰው ታገኙ እንደሆነ ይቅር እላታለሁ።
እናንተ የእስራኤል ልጆች ሆይ! እውነትና ጽኑ ፍቅር አምላክንም ማወቅ በምድሪቱ ስለ ሌለ ጌታ በምድሪቱ ላይ ከሚኖሩ ጋር ሙግት አለውና የጌታን ቃል ስሙ።
አንድ ሦስተኛውን ክፍል ወደ እሳት አስገባለሁ፤ ብርም እንደሚነጥር አነጥራቸዋለሁ፤ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፤ እነርሱም ስሜን ይጠራሉ፥ እኔም እሰማቸዋለሁ፤ እኔም፦ “ይህ ሕዝቤ ነው” እላለሁ፥ እርሱም፦ “ጌታ አምላኬ ነው” ይላል።
ብርን እንደሚያነጥርና እንደሚያጠራ ሰው ይቀመጣል፥ የሌዊንም ልጆች ያጠራል፥ እንደ ወርቅና እንደ ብርም ያነጥራቸዋል፤ እነርሱም ለእግዚአብሔር በጽድቅ ቁርባንን የሚያቀርቡ ይሆናሉ።
በዚህም በእሳት ምንም ቢፈተን ከሚጠፋው ወርቅ ይልቅ አብልጦ የሚከብር የተፈተነ እምነታችሁ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ፥ ለምስጋናና ለክብር ለውዳሴም ይገኝ ዘንድ ነው።