ኤርምያስ 6:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሕዛብ ሆይ! ስለዚህ ስሙ፤ ማኅበር ሆይ! በእነርሱ ምን እንደሚደርስባቸው እወቁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ ሕዝቦች ሆይ ስሙ፤ እናንተም ምስክሮች ምን እንደሚገጥማቸው አስተውሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “እናንተ ሕዝቦች ስሙ! በሕዝቤ ላይ የማደርገውንም ሁሉ አስተውሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሕዛብና የመንጋው ጠባቂዎች ሆይ፥ ስለዚህ ስሙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሕዛብ ሆይ፥ ስለዚህ ስሙ፥ ማኅበር ሆይ፥ እነዚያ የሚያገኛቸውን እወቁ። |
አሕዛብ ሆይ! የጌታን ቃል ስሙ፥ በሩቅም ላሉ ደሴቶች አውጁ፦ “እስራኤልን የበተነ እርሱ ይሰበስበዋል፥ እረኛም መንጋውን እንደሚጠብቅ ይጠብቀዋል” በሉ።
እኔም፦ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! ወዮ፥ አንተ በእውነት ሰይፍ እስከ ነፍስ ድረስ በደረሰ ጊዜ፦ ‘ሰላም ይሆንላችኋል’ ብለህ ይህን ሕዝብና ኢየሩሳሌምን እጅግ አታለልህ” አልሁ።
ሕዝቤ ሆይ፥ የሞዓብ ንጉሥ ባላቅ ያቀደውን፥ የቤዖር ልጅ በለዓም የመለሰለትን፥ የጌታን ጽድቅ እንድታውቅ ከሺጢም ጀምሮ እስከ ጌልገላ ድረስ የሆነውን እባክህን አስታውስ።