La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 51:60 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በባቢሎንም ላይ የሚመጣውን ክፉ ነገር ሁሉ፥ ስለ ባቢሎን የተጻፈውን ይህን ቃል ሁሉ፥ ኤርምያስ በመጽሐፍ ላይ ጻፈው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ኤርምያስ ስለ ባቢሎን ጽፎ ያስቀመጠውን ሁሉ፣ በባቢሎን ላይ የሚመጣውን ጥፋት ሁሉ በብራና ጥቅልል ላይ ጻፈው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በባቢሎን ላይ የሚመጣውን ጥፋት እንዲሁም ስለ እርስዋ የተነገረውን ቃል በመጽሐፍ ጻፍኩ፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሠራ​ያም የቤቱ አዛዥ ነበረ፤ በባ​ቢ​ሎ​ንም ላይ የሚ​መ​ጣ​ውን ክፉ ነገር ሁሉ፥ ስለ ባቢ​ሎን የተ​ጻ​ፈ​ውን ይህን ቃል ሁሉ ኤር​ም​ያስ በአ​ንድ መጽ​ሐፍ ላይ ጻፈው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በባቢሎንም ላይ የሚመጣውን ክፉ ነገር ሁሉ፥ ስለ ባቢሎን የተጻፈውን ይህን ቃል ሁሉ፥ ኤርምያስ በመጽሐፍ ላይ ጻፈው።

Ver Capítulo



ኤርምያስ 51:60
11 Referencias Cruzadas  

አሁንም ሂድ፥ ለሚመጣውም ዘመን ለዘለዓለም እንዲሆን በሰሌዳ ላይ በመጽሐፍም ውስጥ ጻፍላቸው።


ኤርምያስም ሌላ ክርታስ ወሰደ፥ ለኔርያም ልጅ ለጸሐፊው ለባሮክ ሰጠው፤ እርሱም የይሁዳ ንጉሥ ኢዮአቄም በእሳት ያቃጠለውን የመጽሐፉን ቃላት ሁሉ ኤርምያስ እየነገረው ጻፈበት፥ ደግሞም እንደ ቀድሞው ያለ ተመሳሳይ ብዙ ቃላት ተጨመረበት።


ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በባቢሎን ላይና በሌብ-ቃምያ በሚኖሩት ላይ አጥፊውን ነፋስ አስነሣለሁ።


ኤርምያስም ሠራያን እንዲህ አለው፦ “ወደ ባቢሎን በገባህ ጊዜ ልብ ብለህ ይህን ቃል ሁሉ አንብብና፥


እንዲሁም “የምታየውን በመጽሐፍ ጽፈህ ወደ ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ማለትም ወደ ኤፌሶንና ወደ ሰምርኔስ ወደ ጴርጋሞንም ወደ ትያጥሮንም ወደ ሰርዴስም ወደ ፊላደልፊያም ወደ ሎዲቅያም ላክ፤ አለኝ።”


እንግዲህ ያየኸውን አሁንም ያለውን ከዚህም በኋላ የሚሆነውን ጻፍ።