ርስቴን የምትበዘብዙ እናንተ ሆይ! ደስ ቢላችሁ፥ ሐሤትንም ብታደርጉ፥ በማበራየት ላይም እንዳለች ጊደር ብትፈነጩ፥ እንደ ብርቱዎችም ፈረሶች ብታሽካኩ እንኳ፥
ኤርምያስ 51:49 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለባቢሎን በምድሪቱ ሁሉ ተወግተው የሞቱት ወድቀዋል እንዲሁ ለእስራኤል ተወግተው ለሞቱት ባቢሎን መውደቅ አለባት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በምድር ሁሉ የታረዱት፣ በባቢሎን ምክንያት እንደ ወደቁ፣ ባቢሎንም በእስራኤል በታረዱት ምክንያት መውደቅ ይገባታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባቢሎን ለዓለም ሕዝብ እልቂት ምክንያት ሆናለች፤ ለብዙ እስራኤላውያን እልቂት ምክንያት በመሆንዋም እነሆ ባቢሎን ራስዋ መውደቅ አለባት፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባቢሎንም በእስራኤል ስለ ተገደሉት ትወድቃለች፤ ስለ ባቢሎንም በምድር ሁሉ የተገደሉት ይወድቃሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባቢሎንም ከእስራኤል ተወግተው የሞቱት እንዲወድቁ እንዳደረገች፥ እንዲሁ በባቢሎን ከምድሩ ሁሉ ተወግተው የሞቱት ይወድቃሉ። |
ርስቴን የምትበዘብዙ እናንተ ሆይ! ደስ ቢላችሁ፥ ሐሤትንም ብታደርጉ፥ በማበራየት ላይም እንዳለች ጊደር ብትፈነጩ፥ እንደ ብርቱዎችም ፈረሶች ብታሽካኩ እንኳ፥
ቀስትን የሚገትሩትን ቀስተኞችን ሁሉ በባቢሎን ላይ ጥሩአቸው፤ በዙሪያዋ ስፈሩባት አንድም ሰው አያምልጥ፤ በእስራኤል ቅዱስ በጌታ ላይ በኩራት አልታዘዝም ብላለችና እንደ ሥራዋ መጠን መልሱላት፥ እንዳደረገችም ሁሉ አድርጉባት።
በጽዮን የሚኖሩ እንዲህ ይበሉ፦ “በእኔና በሥጋ ዘመዶቼ ላይ የተደረገ ግፍ በባቢሎን ላይ ይሁን” ኢየሩሳሌምም እንዲህ ትበል፦ “ደሜ በከለዳውያን ምድር በሚኖሩት ላይ ይሁን”።
አዶኒቤዜቅም፥ “የእጃቸውና የእግራቸው አውራ ጣቶች የተቈረጡባቸው ሰባ ነገሥታት ከገበታዬ ሥር የወደቀ ፍርፋሪ ይለቃቅሙ ነበር፤ አሁን ግን እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ የፈጸምሁትን አመጣብኝ” አለ፤ እነርሱም ወደ ኢየሩሳሌም አመጡት፤ በዚያም ሞተ።