ከፍ ከፍ ብሎ የነበረውንም ይህን ቤት እያዩ በዚያ የሚያልፉ ሰዎች ሁሉ፦ ‘ጌታ በዚህ አገርና በዚህ ቤት ለምን እንዲህ አደረገ?’ ብለው ይደነቃሉ።
ኤርምያስ 51:41 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሼሻክ እንዴት ተያዘች! ምድርም ሁሉ የሚያመሰግናት እንዴት ተወሰደች! ባቢሎንም በአሕዛብ መካከል መሣቀቅያ እንዴት ሆነች! አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሼሻክ እንዴት ተማረከች! የምድር ሁሉ ትምክሕትስ እንዴት ተያዘች! ባቢሎን በሕዝብ ሁሉ ዘንድ፣ ምንኛ አስደንጋጭ ሆነች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የባቢሎን ከተማ እንዴት ተወረረች! ያቺ የዓለም መመኪያ የነበረችው እርስዋ እንዴት ተያዘች! ባቢሎንስ በሕዝብ ዘንድ ምንኛ አስደንጋጭ ሆነች! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የምድርም ሁሉ ክብር እንዴት ተያዘች! እንዴትስ ተወሰደች! ባቢሎን በአሕዛብ መካከል እንዴት ለጥፋት ሆነች! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሼሻክ እንዴት ተያዘች! የምድርም ሁሉ ምስጋና እንዴት ተወሰደች! ባቢሎንም በአሕዛብ መካከል መደነቂያ እንዴት ሆነች! |
ከፍ ከፍ ብሎ የነበረውንም ይህን ቤት እያዩ በዚያ የሚያልፉ ሰዎች ሁሉ፦ ‘ጌታ በዚህ አገርና በዚህ ቤት ለምን እንዲህ አደረገ?’ ብለው ይደነቃሉ።
አንዱን ከሌላው በመቀጠል፥ ቅርብና ሩቅ የሰሜን ነገሥታትንም ሁሉ፥ በምድር ፊት ላይ ያሉ የዓለም መንግሥታትንም ሁሉ አጠጣኋቸው፤ የሼሻክም ንጉሥ ከእነርሱ በኋላ ይጠጣል።