ደግሞም የካህናቱ አለቆች ሁሉ ሕዝቡም እንደ አሕዛብ ያለ ርኩሰት ሁሉ በመከተል መተላለፍን አበዙ፤ በኢየሩሳሌምም ጌታ ራሱ የቀደሰውን የጌታን ቤት አረከሱ።
ኤርምያስ 5:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ታላላቆቹ እሄዳለሁ እነርሱንም አናግራቸዋለሁ፤ የጌታን መንገንድና የአምላካቸውን ሕግ ያውቃሉና” አልሁ። እነዚህ ግን ቀንበሩን በአንድነት ሰብረዋል፥ እስራቱንም ቈርጠዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ወደ ታላላቆቹ እሄዳለሁ፤ ለእነርሱም እናገራለሁ፤ በርግጥ እነርሱ የእግዚአብሔርን መንገድ፣ የአምላካቸውንም ሕግ ያውቃሉና።” ነገር ግን እነርሱም ቢሆኑ ያው እንደዚያው ቀንበሩን ሰብረዋል፤ እስራቱንም በጥሰዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲህ በሥልጣን ላይ ወዳሉት ገዢዎች ሄጄ፥ ከእነርሱ ጋር እነጋገራለሁ፤ በእርግጥ እነርሱ የእግዚአብሔርን መንገድና የአምላካቸውን ሕግ ያውቃሉ፤” ነገር ግን እነርሱም ቢሆኑ በእግዚአብሔር ላይ ዐምፀዋል፤ ለእርሱም መታዘዝ እምቢ ብለዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ታላላቆቹ እሄዳለሁ እናገራቸውማለሁ፤ እነርሱ የእግዚአብሔርን መንገድና የአምላካቸውን ፍርድ ያውቃሉና።” እነዚህ ግን ቀንበሩን በአንድነት ሰብረዋል፤ እስራቱንም ቈርጠዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ታላላቆቹ እሄዳለሁ እናገራቸውማለሁ፥ የእግዚአብሔርን መንገንድና የአምላካቸውን ሕግ ያውቃሉና አልሁ። እነዚህ ግን ቀንበሩን በአንድነት ሰብረዋል፥ እስራቱንም ቈርጠዋል። |
ደግሞም የካህናቱ አለቆች ሁሉ ሕዝቡም እንደ አሕዛብ ያለ ርኩሰት ሁሉ በመከተል መተላለፍን አበዙ፤ በኢየሩሳሌምም ጌታ ራሱ የቀደሰውን የጌታን ቤት አረከሱ።
ገዥዎችሽ ዐመፀኞችና የሌባ ግብረ ዐበሮች ናቸው፤ ሁሉም ጉቦን ይወዳሉ፤ እጅ መንሻንም በብርቱ ይፈልጋሉ፤ አባት ለሌላቸው አይቆሙም፤ የመበለቶችንም አቤቱታ አይሰሙም።
“ከጥንት ጀምሮ ቀንበርሽን ሰብረሻል እስራትሽንም በጥሰሻል፤ አንቺም፦ ‘አላገለግልም’ አልሽ፥ ነገር ግን ከፍ ባለው ኮረብታ ሁሉ ላይ ከለምለምም ዛፍ ሁሉ በታች ለማመንዘር ተጋደምሽ።
ትውልድ ሆይ! የጌታን ቃል ተመልከቱ። በውኑ ለእስራኤል ምድረ በዳ ወይስ የጨለመች ምድር ሆንኩባትን? ሕዝቤስ ስለምን፦ ‘እኛ ፈርጥጠናል፤ ዳግመኛ ወደ አንተ አንመጣም’ ይላሉ?
ውሽሞችህ ሁሉ ረስተውሃል አይፈልጉህምም፤ በደልህ ታላቅ ስለሆነ ኃጢአትህም ስለ በዛ፥ ጨካኝ ሰው እንደሚቀጣው ጠላትም እንደሚያቆስለው አቁስዬሃለሁና።
“ከታናናሾቻቸው ጀምሮ እስከ ታላላቆቻቸ ድረስ ሁሉም በግፍ ለሚገኝ ጥቅም ስስታም ናቸውና፥ ከነቢዩም ጀምሮ እስከ ካህኑ ድረስ ሁሉም ተንኰልን ይፈጽማሉ።
ምላሳቸውን ስለ ሐሰት እንደ ቀስት ገተሩ፤ በምድር በረቱ ነገር ግን ለእውነት አይደለም፤ ከክፋት ወደ ክፋት ይሄዳሉና፥ እኔንም አላወቁምና፥ ይላል ጌታ።
“እናንተ በሰማርያ ተራራ ያላችሁ፥ ድሆችንም የምትበድሉ፥ ችግረኛውንም የምትጨቁኑ፥ ጌቶቻቸውንም፦ ‘አምጡ እንጠጣ’ የምትሉ እናንተ የባሳን ላሞች ሆይ! ይህን ቃል ስሙ።
አለቆችዋ በጉቦ ይፈርዳሉ፥ ካህናቷ በክፍያ ያስተምራሉ፥ ነቢዮችዋ በብር ያሟርታሉ፤ “ጌታ በመካከላችን አይደለምን? ክፉ ነገር በእኛ ላይ አይመጣብንም” እያሉ በጌታ ይደገፋሉ።