La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 49:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ወይን ለቃሚዎች ቢመጡብህ፥ ቃርሚያውን አይተዉልህምን? ሌቦችስ በሌሊት ቢመጡ፥ የሚዘርፉት የሚበቃቸውን ያህል አይደለምን?

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ወይን ለቃሚዎች ወደ አንተ ቢመጡ፣ ጥቂት ወይን አያስቀሩምን? ሌቦችስ በሌሊት ቢመጡ፣ የሚሰርቁት የሚፈልጉትን ብቻ አይደለምን?

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሰዎች የወይን ዘለላ በሚለቅሙበት ጊዜ በወይኑ ተክል ላይ ጥቂት ቃርሚያ ይተዋሉ፤ ወንበዴዎችም በሌሊት በመጡ ጊዜ የሚፈልጉትን ያኽል ብቻ ይወስዳሉ፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ወይን ለቃ​ሚ​ዎች ቢመ​ጡ​ብህ፥ ቃር​ሚ​ያ​ውን አይ​ተ​ዉ​ል​ህ​ምን? ሌቦ​ችስ በሌ​ሊት ቢመጡ፥ የሚ​ያ​ጠ​ፉት እስ​ኪ​በ​ቃ​ቸው ድረስ አይ​ደ​ለ​ምን?

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ወይን ለቃሚዎች ቢመጡብህ፥ ቃርሚያውን አይተውልህምን? ሌቦችስ በሌሊት ቢመጡ፥ የሚያጠፉት እስኪበቃቸው ድረስ አይደለምን?

Ver Capítulo



ኤርምያስ 49:9
4 Referencias Cruzadas  

የወይራ ዛፍ ሲያራግፉት በቅርንጫፉ ራስ ላይ ሁለት ወይም ሦስት ፍሬ እንደሚቀር፥ አራት ወይም አምስት ፍሬ ችፍግ ባለው ቅርንጫፍ ላይ እንደሚገኝ፥ እንዲሁ ጥቂት ቃርሚያ ይቀራል፥ ይላል ጌታ የእስራኤል አምላክ።


የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ሰው ወይኑን እንደሚለቅም፥ እንዲሁ ከእስራኤል የተረፉትን ፈጽሞ ይለቅሙአችኋል፤ እጅህንም እንደ ለቃሚ በቅርንጫፎቹ ላይ ዳግመኛ ዘርጋ።”


“የምድራችሁንም መከር በምትሰበስቡበት ጊዜ እስከ እርሻችሁ ድንበር ድረስ ፈጽማችሁ አትሰብስቡ፥ የመከሩንም ቃርሚያ አትልቀሙ።