ኤርምያስ 49:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሦርም የቀበሮዎች መኖሪያና የዘለዓለም ባድማ ትሆናለች፤ በዚያም ማንም ሰው አይኖርም፥ የሰው ልጅም አይቀመጥባትም።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሐጾር የቀበሮዎች መፈንጫ፣ ለዘላለም ባድማ ትሆናለች፤ ማንም በዚያ አይኖርም፤ የሚቀመጥባትም አይገኝም።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም ሐጾር ለዘለዓለሙ ቀበሮዎች ብቻ የሚኖሩባት ምድረ በዳ ሆና ትቀራለች፤ ዳግመኛም በዚያ ሰፍሮ የሚኖር ሕዝብ ከቶ አይገኝም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሦርም የወፎች መኖሪያና የዘለዓለም ባድማ ትሆናለች፤ በዚያም ሰው አይኖርም፤ የሰው ልጅም አይቀመጥባትም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሶርም የቀበሮ መኖሪያና የዘላለም ባድማ ትሆናለች፥ በዚያም ሰው አይኖርም፥ የሰው ልጅም አይቀመጥባትም። |
ስለዚህ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ እኔ ሕያው ነኝና ሞዓብ እንደ ሰዶም፥ የአሞንም ልጆች እንደ ገሞራ ይሆናሉ፥ አረም እንደ ዋጠው ስፍራና እንደ ጨው ጉድጓድ ለዘለዓለምም ይጠፋሉ፤ የሕዝቤም ትሩፍ ይበዘብዛቸዋል፥ ከወገኔም የተረፉት ይወርሱአቸዋል።
በብርቱም ድምፅ “ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች! ወደቀች! የአጋንንትም ማደሪያ ሆነች፤ የርኩሳንም መናፍስት ሁሉ መጠጊያ የርኩሳንና የተጠሉም ወፎች ሁሉ መጠጊያ ሆነች፤