ኤርምያስ 49:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በደማስቆም ቅጥር ላይ እሳት አነድዳለሁ የወልደ አዴርንም የንጉሥ ቅጥሮች ትበላለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በደማስቆ ቅጥር ላይ እሳት እለኵሳለሁ፤ የቤን ሃዳድንም ዐምባ ይበላል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የደማስቆን ቅጽር ሁሉ በእሳት አጋያለሁ፤ የንጉሥ ቤንሀዳድንም ቤተ መንግሥት በእሳት አቃጥላለሁ፤ እኔ የሠራዊት አምላክ ይህን ተናግሬአለሁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በደማስቆም ቅጥር ላይ እሳት አነድዳለሁ፤ የወልደ አዴርንም አዳራሾች ትበላለች።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በደማስቆም ቅጥር ላይ እሳት አነድዳለሁ የወልደ አዴርንም አዳራሾች ትበላለች። |
በግብጽም አማልክት ቤቶች እሳትን አነድዳለሁ፤ የባቢሎንም ንጉሥ ያቃጥላቸዋል ይማርካቸዋልም፤ እረኛም ደበሎውን እንደሚደርብ እንዲሁ የግብጽን አገር ይደርባል፤ ከዚያም ስፍራ በሰላም ይወጣል።