ኤርምያስ 49:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከጌታ ዘንድ መልእክት ሰምቻለሁ በአሕዛብም መካከል፦ “ተሰብሰቡ፥ በእርሷም ላይ ኑ ለጦርነትም ተነሡ” የሚል መልእክተኛ ተልኮአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእግዚአብሔር ዘንድ መልእክት ሰምቻለሁ፤ “እርሷን ለመውጋት ተሰብሰቡ፤ ለጦርነትም ውጡ” የሚል መልእክተኛ ወደ አሕዛብ ተልኳል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ መልእክት ከእግዚአብሔር ሰምቼአለሁ፤ “በኤዶም ሕዝብ ላይ አደጋ ለመጣል ተሰብሰቡ! ለጦርነትም ተነሡ!” ብሎ የሚናገር መልእክተኛ ወደ ሕዝቦች ተልኮአል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ከእግዚአብሔር ዘንድ መስማትን ሰምቻለሁ፤ በአሕዛብ ሀገሮች ተሰብሰቡ፤ በእርስዋም ላይ ኑ፤ እርስዋንም ውጓት፥ የሚል መልእክተኛ ተልኳል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእግዚአብሔር ዘንድ ወሬ ሰምቻለሁ በአሕዛብም መካከል፦ ተሰብሰቡ፥ በእርስዋም ላይ ኑ ለሰልፍም ተነሡ የሚል መልእክተኛ ተልኮአል። |
እነሆ፥ በላዩ መንፈስን እሰድዳለሁ፥ ወሬም ይሰማል፥ ወደ ምድሩም ይመለሳል፤ በምድሩም ላይ በሰይፍ እንዲወድቅ አደርጋለሁ በሉት’ ” አላቸው።
ፍላጾችን ሳሉ ጋሻዎችንም አንሡ፤ ጌታ ሊያጠፋት አሳቡ በባቢሎን ላይ ነውና የሜዶንን ነገሥታት መንፈስ አስነሥቶአል፤ የጌታ በቀል ስለ መቅደሱ ሲል የሚበቀለው በቀል በእርሷ ላይ ነውና።
በምድሪቱም ከሚሰማው ወሬ የተነሣ ልባችሁ የዛለ አይሁን አትፍሩም፤ በአንዱም ዓመት አንድ ወሬ፥ በሚቀጥለውም ዓመት ሌላ ወሬ ይመጣል፥ በምድሪቱም ላይ ዓመጽ ይሆናል፥ ገዢም በገዢ ላይ ይነሣል።