ኤርምያስ 48:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተ በሞዓብ የምትኖሩ ሆይ! ከተሞችን ትታችሁ በዓለት ንቃቃት መካከል ተቀመጡ፥ በገደል አፋፍም ቤትዋን እንደምትሠራ እንደ ርግብ ሁኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ በሞዓብ የምትኖሩ ሆይ፤ ከከተማ ወጥታችሁ በዐለት መካከል ኑሩ፤ በገደል አፋፍ ላይ ጐጆዋን እንደምትሠራ፣ እንደ ርግብ ሁኑ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የሞአብ ነዋሪዎች ሆይ! ከተሞቻችሁን ለቃችሁ በገደል አፋፍ ጎጆዋን እንደምትሠራ እንደ ርግብ በመሆን በቋጥኞች መካከል ኑሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሞአብ የሚኖሩ ከተሞችን ትተው በዓለት ውስጥ ተቀመጡ፤ በገደል አፋፍም ቤቷን እንደምትሠራ እንደ ርግብ ሆኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተ በሞዓብ የምትኖሩ ሆይ፥ ከተሞችን ትታችሁ በዓለት ውስጥ ተቀመጡ፥ በገደል አፋፍም ቤትዋን እንደምትሠራ እንደ ርግብ ሁኑ። |
በዓለት ንቃቃት ውስጥ የምትቀመጥ፥ የተራራውን ከፍታ የምትይዝ ሆይ! ማሣቀቅያህና የልብህ ኩራት አታልለውሃል። ምንም እንኳ ጎጆህን እንደ ንስር ጎጆ ከፍ ብታደርግ፥ ከዚያ አወርድሃለሁ፥ ይላል ጌታ።
የዔሳውን ጥፋት እርሱን በምጐበኝበት ጊዜ አመጣበታለሁና፥ እናንተ በድዳን የምትኖሩ ሆይ! ሽሹ፥ ወደ ኋላ ተመለሱ፥ በጥልቅም ውስጥ ተቀመጡ።
እስራኤላውያን ያሉበት ሁኔታ እጅግ አስጊ መሆኑንና ሠራዊታቸውም በከባድ ጭንቀት ውስጥ መግባቱን ባዩ ጊዜ፥ በየዋሻውና በየቁጥቋጦው፥ በየዐለቱ መካከልና በየገደሉ እንዲሁም በየጉድጓዱ ሁሉ ተሸሸጉ።