ኤርምያስ 46:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጋሻንና አላባሽን አዘጋጁ ወደ ጦርነትም ቅረቡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ትልቁንና ትንሹን ጋሻ አዘጋጁ፤ ለውጊያም ውጡ! አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ጋሻችሁን አዘጋጁ፤ ወደ ጦር ሜዳም ዝመቱ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ጋሻና ጦር ያዙ፤ ወደ ሰልፍም ቅረቡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጋሻ ጦር አዘጋጁ ወደ ሰልፍም ቅረቡ። |
በግብጽ አውጁ፥ በሚግዶልም አሰሙ፥ በሜምፎስና በጣፍናስ አሰሙ፤ እናንተም፦ ሰይፍ በዙሪያህ ያለውን በልቶአልና ተነሥ ራስህንም አዘጋጅ በሉ።
እነሆ፥ መልካም ዜና የሚያመጣ፥ ሰላምንም የሚያሰማ ሰው እግር በተራሮች ላይ ነው! ይሁዳ ሆይ በዓሎችሽን አክብሪ፥ ስእለቶችሽን ክፈዪ፤ አጥፊው ፈጽሞ ተቆርጧልና፥ ከእንግዲህም ወዲህ በአንቺ በኩል አያልፍምና።