ኤርምያስ 46:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱ ስፍር ቊጥር የላቸውምና ከአንበጣም ይልቅ ብዙ ናቸውና የማያሳልፍ ጥቅጥቅ ቢሆንም እንኳ የዱርዋን ዛፎች ይቈርጣሉ፥ ይላል ጌታ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጥቅጥቅ ጫካ ቢሆንም፣ ደኗን ይመነጥራሉ፤” ይላል እግዚአብሔር፤ “ብዛታቸው እንደ አንበጣ ነው፤ ሊቈጠሩም አይችሉም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሊቈጠሩ የማይችሉ የዱርዋን ዛፎች ይቈርጣሉ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ከአንበጣ ይልቅ በዝተዋልና፥ ቍጥርም የላቸውምና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይቈጠሩ ዘንድ የማይቻሉትን የዱርዋን ዛፎች ይቈርጣሉ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ ከአንበጣ ይልቅ በዝተዋልና ቍጥርም የላቸውምና። |
ከብቶቻቸውንና ድንኳኖቻቸውን ይዘው ሲመጡ ልክ የአንበጣ መንጋ ይመስሉ ነበር፤ ሰዎቹንም ሆነ ግመሎቻቸውን ለመቁጠር አዳጋች ሲሆን፥ የሚመጡትም ምድሪቱን ለማጥፋት ነበር።
ብዛታቸው እንደ አንበጣ መንጋ የሆነ ምድያማውያን፥ አማሌቃውያንና ሌሎችም የምሥራቅ ሕዝቦች በሸለቆው ውስጥ ሰፍረው ነበር፤ የግመሎቻቸውም ብዛት በባሕር ዳርቻ እንዳለ አሸዋ ስፍር ቍጥር አልነበረውም።