La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 46:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እርሱም ብዙዎችን አሰነካከለ፥ እርሱም ደግሞ ወደቀ፤ እርስ በርሳቸውም፦ ተነሡ፥ የአስጨናቂው ሰው ከሆነው ሰይፍ ፊት ወደ ወገናችን ወደ ተወለድንባትም ምድር እንመለስ ተባባሉ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ደጋግመው ይሰናከላሉ፣ አንዱም በሌላው ላይ ይወድቃል፤ ‘ተነሡ እንሂድ፤ ወደ ሕዝባችንና ወደ ትውልድ አገራችን እንመለስ፤ ከጠላትም ሰይፍ እናምልጥ’ ይላሉ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ጀሌዎቻቸው ተሰናክለው አንዱ በአንዱ ላይ ይወድቃሉ፤ እርስ በርሱም አንዱ ሌላውን፥ ‘ከጠላት ሰይፍ አምልጠን ከሀገራችን ሕዝብ መቀላቀል እንድንችል እንፍጠን’ ይለዋል።”

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ብዛ​ታ​ቸ​ውም ደከመ፤ ወደ​ቀም፤ አን​ዱም አንዱ ለጓ​ደ​ኛው፦ ተነሥ፤ ከአ​ረ​ማ​ው​ያን ሰይፍ ፊት ወደ ወገ​ና​ችን ወደ ተወ​ለ​ድ​ን​ባት ምድር እን​መ​ለስ አለው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ብዛታቸውም ተሰናከለ፥ ሰውም አንዱ በአንዱ ላይ ወደቀ፥ እነርሱም፦ ተነሡ፥ ከሚያስጨንቅ ሰይፍ ፊት ወደ ወገናችን ወደ ተወለድንባት ምድር እንመለስ አሉ።

Ver Capítulo



ኤርምያስ 46:16
5 Referencias Cruzadas  

በእርሷም መካከል ያሉ ቅጥረኛ ወታደሮችዋ እንደ ሰቡ ወይፈኖች ናቸው፤ የጥፋታቸው ቀንና የመጐብኘታቸው ጊዜ መጥቶባቸዋልና ተመለሱ፥ በአንድነትም ሸሹ፥ አልቆሙምም።


ፈጣኑ መሸሽ አይችልም ኃያሉም አያመልጥም፤ በሰሜን በኩል ባለው በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ እነርሱ ተሰናክለው ወደቁ።


ዘሪውንና በመከር ጊዜ ማጭድ የሚይዘውን ከባቢሎን አጥፉ፤ የአስጨናቂው ሰው ከሆነው ሰይፍ ፊት እያንዳንዱ ወደ ወገኑ ይመለሳል እያንዳንዱም ወደ አገሩ ይሸሻል።


ባቢሎንን ልንፈውሳት ሞከርን፥ እርሷ ግን አልተፈወሰችም፤ ፍርድዋ እስከ ሰማይ ደርሶአልና፥ እስከ ደመናም ድረስ ከፍ ከፍ ብሏልና ትታችኋት እያንዳንዳችን ወደ አገራችን እንሂድ።