ንጉሡም አሳ የይሁዳን ሰዎች ሁሉ ሰበሰበ፤ እነርሱም ባኦስ ይሠራበት የነበረውን የራማን ድንጋይና እንጨት ወሰዱ፥ እርሱም ጌባንና ምጽጳን ሠራበት።
ኤርምያስ 40:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤርምያስም የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ወዳለበት ወደ ምጽጳ ሄደ፥ በአገሩም ውስጥ በቀሩት ሕዝብ መካከል ከእርሱ ጋር ተቀመጠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኤርምያስም የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ወዳለበት ወደ ምጽጳ ሄደ፤ ከርሱም ጋራ በምድሪቱ በቀረው ሕዝብ መካከል ኖረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔም ከገዳልያ ጋር ለመኖር ወደ ምጽጳ ሄድኩ፤ እዚያም በምድሪቱ ላይ በቀሩት ሕዝብ መካከል አብሬ ኖርኩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤርምያስም የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ወደ አለበት ወደ መሴፋ ሄደ፤ ከእርሱም ጋር በሀገሩ ውስጥ በቀሩት ሕዝብ መካከል ተቀመጠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኤርምያስም የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ወዳለበት ወደ ምጽጳ ሄደ፥ ከእርሱም ጋር በአገሩ ውስጥ በቀሩት ሕዝብ መካከል ተቀመጠ። |
ንጉሡም አሳ የይሁዳን ሰዎች ሁሉ ሰበሰበ፤ እነርሱም ባኦስ ይሠራበት የነበረውን የራማን ድንጋይና እንጨት ወሰዱ፥ እርሱም ጌባንና ምጽጳን ሠራበት።
ልከው ኤርምያስን ከእስር ቤት አደባባይ አወጡት፤ ወደ ቤቱም እንዲወስደው ለሳፋን ልጅ ለአኪቃም ልጅ ለጎዶልያስ ሰጡት፤ እርሱም በሕዝብ መካከል ተቀመጠ።
በሰባተኛውም ወር ከመንግሥት ወገንና ከንጉሡ ዋና ዋና ሹማምንት አንዱ የሆነው የኤሊሳማ ልጅ የናታንያ ልጅ እስማኤል፥ ከዐሥር ሰዎች ጋር ሆኖ ወደ ምጽጳ ወደ አኪቃም ልጅ ወደ ጎዶልያስ መጣ፤ በዚያም በምጽጳ በአንድ ላይ እንጀራ እየበሉ ሳሉ፥
ከዚያም ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ያሉ እንዲሁም በገለዓድ ምድር የሚገኙ እስራኤላውያን ሁሉ እንደ አንድ ሰው ሆነው ወጡ፤ በምጽጳም በጌታ ፊት ተሰበሰቡ።