ሰዎቹ ግን፥ “አንተ መውጣት የለብህም፤ እንድንሸሽ ብንገደድ፥ ስለኛ ምንም አይገዳቸውም፤ ግማሾቻችን እንኳ ብንሞት፥ ስለኛ ምንም አይገዳቸውም፤ አንተ ግን ብቻህን ከእኛ ከዐሥሩ ሺህ ትበልጣለህ! ስለዚህ በከተማ ሆነህ ብትረዳን ይሻላል” አሉት።
ኤርምያስ 40:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቃሬያም ልጅ ዮሐናን፦ “እባክህ፥ ልሂድ፤ ማንም ሳያውቅ የናታንያን ልጅ እስማኤልን ልግደለው፤ ወደ አንተ የተሰበሰቡ አይሁድ ሁሉ እንዲበተኑ፥ የይሁዳም ትሩፍ እንዲጠፋ አንተን ለምን ይገድላል?” ብሎ በምጽጳ በድብቅ ለጎዶልያስ ተናገረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቃሬያ ልጅ ዮሐናን፣ “ማንም ሳያውቅ የናታንያን ልጅ እስማኤልን ሄጄ ልግደለው፤ ሸሽተው ወደ አንተ የመጡት አይሁድ እንዲበተኑ፣ በይሁዳም የቀሩት እንዲጠፉ ለምን ይገድልሃል?” ብሎ በምጽጳ ለጎዶልያስ በምስጢር ነገረው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ ዮሐናን በምጽጳ በግል እንዲህ አለው፦ “ይህን ያደረገ ማን እንደ ሆነ ሳይታወቅ ሄጄ እስማኤልን ልግደለው፤ እንዴት እርሱ አንተን ሊገድልህ ይደፍራል? እርሱ ከገደለህ እኮ በዙሪያህ ለተሰበሰቡት አይሁድ መበታተን ምክንያት ይሆናል፤ በይሁዳ ምድር ከምርኮ በቀሩትም ሕዝብ ላይ ታላቅ ጥፋትን ያመጣል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቃርሔም ልጅ ዮሐናን፥ “እባክህ፥ ልሂድ፤ ማንም ሳያውቅ የናታንያን ልጅ እስማኤልን ልግደለው፤ ወደ አንተ የተሰበሰቡ አይሁድ ሁሉ እንዲበተኑ፥ የይሁዳም ቅሬታ እንዲጠፋ ነፍስህን ስለ ምን ይገድላል?” ብሎ በመሴፋ በቈይታ ለጎዶልያስ ተናገረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቃሬያም ልጅ ዮሐናን፦ እባክህ፥ ልሂድ፥ ማንም ሳያውቅ የናታንያን ልጅ እስማኤልን ልግደለው፥ ወደ አንተ የተሰበሰቡ አይሁድ ሁሉ እንዲበተኑ የይሁዳም ቅሬታ እንዲጠፋ ነፍስህን ስለ ምን ይገድላል? ብሎ በምጽጳ በቆይታ ለጎዶልያስ ተናገረ። |
ሰዎቹ ግን፥ “አንተ መውጣት የለብህም፤ እንድንሸሽ ብንገደድ፥ ስለኛ ምንም አይገዳቸውም፤ ግማሾቻችን እንኳ ብንሞት፥ ስለኛ ምንም አይገዳቸውም፤ አንተ ግን ብቻህን ከእኛ ከዐሥሩ ሺህ ትበልጣለህ! ስለዚህ በከተማ ሆነህ ብትረዳን ይሻላል” አሉት።
የጽሩያ ልጅ አቢሳ ግን ዳዊትን ለመታደግ መጣ፤ ፍልስጥኤማዊውንም መትቶ ገደለው። ከዚያም የዳዊት ሰዎች፥ “የእስራኤል መብራት እንዳይጠፋ ከእንግዲህ አንተ ከእኛ ጋር ወደ ጦርነት መውጣት የለብህም” ብለው ማሉለት።
የናታንያ ልጅ እስማኤል፥ የቃሬያም ልጆች ዮሐናንና ዮናታን፥ የተንሑሜትም ልጅ ሠራያ፥ የነጦፋዊውም የዮፌ ልጆች የማዕካታዊውም ልጅ ያእዛንያ ከሰዎቻቸው ጋር ወደ ጎዶልያስ ወደ ምጽጳ መጡ።
ነቢዩንም ኤርምያስን እንዲህ አሉት፦ “በዐይኖችህ እንደምታየን ከብዙ ጥቂት ተርፈናልና ልመናችን እባክህ፥ በፊትህ ትድረስ፥ ስለ እኛና ስለዚህ ትሩፍ ሁሉ ለጌታ ለአምላክህ ጸልይ፥
ሳኦልም በመንገድ ዳር ወዳለው ወደ አንድ የበጎች ማደሪያ በደረሰ ጊዜ፥ ዋሻ አግኝቶ ወገቡን ሊሞክር ወደዚያ ገባ። ዳዊትና ሰዎቹም ከዋሻው በውስጠኛው ቦታ ተቀምጠው ነበር።
አቢሳም ዳዊትን፥ “ዛሬ እግዚአብሔር ጠላትህን በእጅህ ላይ ጥሎታል፤ አሁንም እኔ አንድ ጊዜ በጦር ወግቼ ከመሬት ጋር ላጣብቀው፤ መድገምም አያስፈልገኝም” አለው።