ኤርምያስ 40:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የአሞን ልጆች ንጉሥ በኣሊስ አንተን ለመግደል የናታንያን ልጅ እስማኤልን እንደ ላከ ፈጽሞ አታውቅምን?” አሉት። የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ግን አላመናቸውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የአሞናውያን ንጉሥ በአሊስ አንተን ለመግደል የናታንያን ልጅ እስማኤልን እንደ ላከው አታውቅምን?” አሉት። የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ግን አላመናቸውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እስማኤል አንተን እንዲገድልህ የዐሞን ንጉሥ በዐሊስ የላከው መሆኑን አታውቅምን?” ብለው ጠየቁት። ገዳልያ ግን ይህን አላመነም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የአሞን ልጆች ንጉሥ በኣሊስ ይገድልህ ዘንድ የናታንያን ልጅ እስማኤልን እንደ ላከ ታውቃለህን?” አሉት። የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ግን አላመናቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአሞን ልጆች ንጉሥ በኣሊስ ይገድልህ ዘንድ የናታንያን ልጅ እስማኤልን እንደ ሰደደ ታውቃለህን? አሉት። የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ግን አላመናቸውም። |
የናታንያ ልጅ እስማኤል፥ የቃሬያም ልጆች ዮሐናንና ዮናታን፥ የተንሑሜትም ልጅ ሠራያ፥ የነጦፋዊውም የዮፌ ልጆች የማዕካታዊውም ልጅ ያእዛንያ ከሰዎቻቸው ጋር ወደ ጎዶልያስ ወደ ምጽጳ መጡ።
በሰባተኛውም ወር ከመንግሥት ወገንና ከንጉሡ ዋና ዋና ሹማምንት አንዱ የሆነው የኤሊሳማ ልጅ የናታንያ ልጅ እስማኤል፥ ከዐሥር ሰዎች ጋር ሆኖ ወደ ምጽጳ ወደ አኪቃም ልጅ ወደ ጎዶልያስ መጣ፤ በዚያም በምጽጳ በአንድ ላይ እንጀራ እየበሉ ሳሉ፥
እስማኤልም በምጽጳ የነበረውን የሕዝቡን ትሩፍ ሁሉ፥ የንጉሡን ሴቶች ልጆች የዘበኞቹም አለቃ ናቡዘረዳን ለአኪቃም ልጅ ለጎዶልያስ የሰጠውን በምጽጳ የቀሩትን ሕዝብ ሁሉ ማረከ፤ የናታንያም ልጅ እስማኤል ማርኮ ወደ አሞን ልጆች ለመሄድ ተነሣ።
የናታንያም ልጅ እስማኤል ከእርሱም ጋር የነበሩት አሥሩ ሰዎች ተነሥተው የሳፋንን ልጅ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በሰይፍ መቱ፥ የባቢሎንም ንጉሥ በአገሩ ላይ የሾመውን ገደሉ።