ኤርምያስ 4:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ እኔ ጽኑ የሆነ ነፋስ ከእነዚህ ይመጣል ይባላል። አሁንም እኔ ደግሞ ፍርዴን በእነርሱ ላይ እናገራለሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእኔ ትእዛዝ ይነፍሳል፤ እንግዲህ ፍርዴን በእነርሱ ላይ እናገራለሁ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእግዚአብሔር ትእዛዝ የሚመጣ ነፋስ ስለ ሆነ ከሁሉ የበረታ ነው፤ ይህን ፍርድ በሕዝቡ ላይ የሚያስተላልፍ ራሱ እግዚአብሔር ነው።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሳች ጋኔን ይመጣል፤ አሁንም እኔ ፍርዴን በእነርሱ ላይ እናገራለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ እኔ ጽኑ የሆነ ነፋስ ከእነዚህ ይመጣል ይባላል። አሁንም እኔ ደግሞ ፍርዴን በእነርሱ ላይ እናገራለሁ። |
ስለ ክፋታቸው ሁሉ ፍርዴን በእነርሱ ላይ እናገራለሁ፥ እኔን ትተውኛል፤ ለሌሎችም አማልክት ዕጣንን አጥነዋል፤ ለእጃቸውም ሥራዎች ሰግደዋልና።
በዚያ ጊዜ ለዚህ ሕዝብና ለኢየሩሳሌም፦ “ለማበጠር ወይም ለማጥራት ሳይሆን የሚያቃጥል ነፋስ በምድረ በዳ ካሉ ከተራቈቱ ኮረብቶች ወደ ወገኔ ሴት ልጅ ይመጣል፤
በወንድሞቹ መካከል ፍሬያማ ቢሆንም እንኳ የምሥራቅ ነፋስ ይመጣል፥ የጌታ ነፋስ ከምድረበዳ ይመጣል፤ ፈሳሹንም ይጠፋል፥ ምንጩንም ይደርቃል፥ የተከበሩ ዕቃዎች ሁሉ ያሉበትን መዝገብ ይበዘብዛል።