በሦስት ቀን ውስጥ በዘጠነኛው ወር ከወሩም በሀያኛው ቀን የይሁዳና የብንያም ሰዎች ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ። ሕዝቡም ሁሉ ስለዚህ ነገርና ስለ ታላቁ ዝናብ እየተንቀጠቀጡ በእግዚአብሔር ቤት ፊት ባለው አደባባይ ተቀመጡ።
ኤርምያስ 36:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡም በዘጠነኛው ወር በክረምት ቤት ተቀምጦ ነበር፥ እፊቱም ባለው ምድጃ ውስጥ እሳት ይነድድ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዘጠነኛው ወር እንደ መሆኑ፣ ንጉሡ የክረምትን ወራት በሚያሳልፍበት ቤት ተቀምጦ ነበር፤ በምድጃ የሚነድድ እሳትም ፊት ለፊቱ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዘጠነኛው ወር ወራቱም ክረምት ስለ ነበረ ንጉሡ የክረምትን ወራት በሚያሳልፍበት ቤተ መንግሥት እሳት በሚነድበት ምድጃ ፊት ለፊት ተቀምጦ ነበር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም በዘጠነኛው ወር በክረምት በሚቀመጥበት ቤት ተቀምጦ ነበር፤ በፊቱም እሳት ይነድድ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም በዘጠነኛው ወር በክረምት ቤት ተቀምጦ ነበር፥ በፊቱም በምድጃ ውስጥ እሳት ይነድድ ነበር። |
በሦስት ቀን ውስጥ በዘጠነኛው ወር ከወሩም በሀያኛው ቀን የይሁዳና የብንያም ሰዎች ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ። ሕዝቡም ሁሉ ስለዚህ ነገርና ስለ ታላቁ ዝናብ እየተንቀጠቀጡ በእግዚአብሔር ቤት ፊት ባለው አደባባይ ተቀመጡ።
እንዲህም ሆነ፤ በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም በአምስተኛው ዓመት በዘጠነኛው ወር፥ የኢየሩሳሌም ሕዝብ ሁሉ ከይሁዳም ከተሞች ወደ ኢየሩሳሌም የመጡት ሕዝብ ሁሉ በጌታ ፊት ለመጾም አዋጅ ነገሩ።
ንጉሡ ሰገነት ላይ ባለው ነፋሻ ዕልፍኝ ውስጥ ብቻውን ተቀምጦ ሳለ ኤሁድ ቀረብ ብሎ፥ “ከእግዚአብሔር ዘንድ ለአንተ ያመጣሁት መልእክት አለኝ” አለው፤ ንጉሡም ከዙፋኑ ተነሣ።