እጃቸውን ያልሰጡ የይሁዳ የጦር መኰንኖችና ወታደሮች የባቢሎን ንጉሥ ገዳልያን ገዢ አድርጎ እንደ ሾመው በሰሙ ጊዜ ወደ ምጽጳ መጥተው ከእርሱ ጋር ተገናኙ፤ እነዚህም የጦር መኰንኖች የነታንያ ልጅ እስማኤል፥ የቃሬሐ ልጅ ዮሐናን፥ የነጦፋ ከተማ ተወላጅ የሆነው የታንሑሜት ልጅ ሠራያና የማዕካ ተወላጅ የሆነው የዛንያ ነበሩ፤
ኤርምያስ 36:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አለቆቹም ሁሉ፦ “በሕዝቡ ጆሮ ያነበብከውን ክርታስ በእጅህ ይዘህ ና” የሚል መልእክት በኲሲ ልጅ በሰሌምያ ልጅ በናታንያ ልጅ በይሁዲ እጅ ወደ ባሮክ ላኩ። የኔርያም ልጅ ባሮክ ክርታሱን በእጁ ይዞ ወደ እነርሱ መጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መኳንንቱ ሁሉ የኩሲን ልጅ የሰሌምያን ልጅ የናታንያን ልጅ ይሁዲን፣ “ለሕዝቡ ያነበብኸውን ብራና ይዘህ እንድትመጣ” ብለው ወደ ባሮክ ላኩ። የኔርያም ልጅ ባሮክ ብራናውን ይዞ ወደ እነርሱ መጣ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ባለ ሥልጣኖቹ ሁሉ ባሮክ ለሕዝቡ ያነበበውን የብራና ጥቅል ይዞ እንዲመጣ ይነግረው ዘንድ ይሁዲን ላኩ፤ (ይሁዲ የነታንያ ልጅ ሲሆን፥ ነታንያ የሸሌምያ ልጅ፥ ሸሌምያም የኩሺ ልጅ ነው፤) ባሮክም የብራናውን ጥቅል ይዞ ወደ እነርሱ መጣ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አለቆቹም ሁሉ፥ “በሕዝቡ ጆሮ ያነበብኸውን ክርታስ በእጅህ ይዘህ ና” ብለው የኩሲ ልጅ የሰሌምያ ልጅ የናታንያ ልጅ ይሁዳን ወደ ኔርዩ ልጅ ወደ ባሮክ ላኩ። የኔርዩም ልጅ ባሮክ ክርታሱን በእጁ ይዞ ወደ እነርሱ ወረደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አለቆቹም ሁሉ፦ በሕዝቡ ጆሮ ያነበብኸውን ክርታስ በእጅህ ይዘህ ና የሚል መልእክት በኵሲ ልጅ በሰሌምያ ልጅ በናታንያ ልጅ በይሁዲ እጅ ወደ ባሮክ ላኩ። የኔርያም ልጅ ባሮክ ክርታሱን በእጁ ይዞ ወደ እነርሱ መጣ። |
እጃቸውን ያልሰጡ የይሁዳ የጦር መኰንኖችና ወታደሮች የባቢሎን ንጉሥ ገዳልያን ገዢ አድርጎ እንደ ሾመው በሰሙ ጊዜ ወደ ምጽጳ መጥተው ከእርሱ ጋር ተገናኙ፤ እነዚህም የጦር መኰንኖች የነታንያ ልጅ እስማኤል፥ የቃሬሐ ልጅ ዮሐናን፥ የነጦፋ ከተማ ተወላጅ የሆነው የታንሑሜት ልጅ ሠራያና የማዕካ ተወላጅ የሆነው የዛንያ ነበሩ፤
“አንድ የመጽሐፍ ክርታስ ውሰድ፥ ለአንተም ከተናገርሁበት ቀን፥ ከኢዮስያስ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በእስራኤልና በይሁዳ ላይ፥ በአሕዛብም ሁሉ ላይ ለአንተ የተናገርሁትን ቃላት ሁሉ ጻፍበት።
ንጉሡም ክርታሱን እንዲያመጣ ይሁዲን ላከ፥ እርሱም ከጸሐፊው ከኤሊሳማ ጓዳ አመጣው፤ ይሁዲም በንጉሡና በንጉሡ አጠገብ በቆሙት አለቆች ሁሉ ጆሮ አነበበው።
የናታንያ ልጅ እስማኤል፥ የቃሬያም ልጆች ዮሐናንና ዮናታን፥ የተንሑሜትም ልጅ ሠራያ፥ የነጦፋዊውም የዮፌ ልጆች የማዕካታዊውም ልጅ ያእዛንያ ከሰዎቻቸው ጋር ወደ ጎዶልያስ ወደ ምጽጳ መጡ።
የቃሬያም ልጅ ዮሐናን የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን ከገደለ በኋላ እርሱና ከእርሱም ጋር የነበሩት የጭፍራ አለቆች ሁሉ ከናታንያ ልጅ ከእስማኤል ከምጽጳ ያስመለሱአቸውን የሕዝቡን ትሩፍ ሁሉ፥ እንዲሁም ከገባዖን ያስመለሱአቸውን ወታደሮች፥ ሴቶችንም፥ ልጆችንም፥ ጃንደረቦችንም፥ ወሰዱ፤
ምክንያቱም የናታንያ ልጅ እስማኤል የባቢሎን ንጉሥ በአገሩ ላይ የሾመውን የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን ስለ ገደለው ከለዳውያንን በመፍራታቸው ነው።
በይሁዳ ንጉሥ በአሞን ልጅ በኢዮስያስ ዘመን ወደ ሕዝቅያስ ልጅ፥ ወደ አማርያ ልጅ፥ ወደ ገዳልያ ልጅ፥ ወደ ኩሺ ልጅ፥ ወደ ሶፎንያስ የመጣ የጌታ ቃል ይህ ነው።