ኢዮስያስ በነገሠ በዐሥራ ስምንተኛው ዓመት የመሹላም የልጅ ልጅ፥ የአጻልያ ልጅ የሆነውን የቤተ መንግሥቱ ጸሐፊ ሳፋንን ከዚህ የሚከተለውን መልእክት ወደ ቤተ መቅደስ ላከው፤
ኤርምያስ 36:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሳፋንም ልጅ የገማርያ ልጅ ሚክያስ የጌታን ቃላት ሁሉ ከመጽሐፉ በሰማ ጊዜ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሳፋን ልጅ የገማርያ ልጅ ሚክያስ ከብራናው የተነበበውን የእግዚአብሔርን ቃል ሁሉ በሰማ ጊዜ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሳፋን የልጅ ልጅ የነበረው የገማርያ ልጅ ሚክያስ እግዚአብሔር የተናገረውን ቃል ሁሉ ባሮክ ከብራናው ሲያነብ ሰማ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሳፋንም ልጅ የገማርያ ልጅ ሚክያስ የእግዚአብሔርን ቃል ሁሉ ከመጽሐፉ ሰማ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሳፋንም ልጅ የገማርያ ልጅ ሚክያስ የእግዚአብሔርን ቃል ሁሉ ከመጽሐፉ በሰማ ጊዜ፥ |
ኢዮስያስ በነገሠ በዐሥራ ስምንተኛው ዓመት የመሹላም የልጅ ልጅ፥ የአጻልያ ልጅ የሆነውን የቤተ መንግሥቱ ጸሐፊ ሳፋንን ከዚህ የሚከተለውን መልእክት ወደ ቤተ መቅደስ ላከው፤
የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር የሳፋን የልጅ ልጅ የአሒቃም ልጅ ገዳልያን ወደ ባቢሎን ተማርከው ሳይወሰዱ ለቀሩት ሰዎች ሁሉ ኃላፊ ይሆን ዘንድ የይሁዳ ገዢ አድርጎ ሾመው።
ንጉሡም ኬልቅያስን፥ የሳፋንንም ልጅ አኪቃምን፥ የሚክያስንም ልጅ ዓብዶንን፥ ጸሐፊውንም ሳፋንን፥ የንጉሡንም ብላቴና ዓሳያን እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፦
ባሮክም የኤርምያስን ቃላት በላይኛው አደባባይ በጌታ ቤት በአዲሱ በር መግቢያ ባለው በጸሐፊው በሳፋን ልጅ፥ በገማርያ ጓዳ በጌታ ቤት ውስጥ በሕዝቡ ሁሉ ጆሮ ከመጽሐፉ አነበበ።