La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 34:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ነገር ግን፥ የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ ሆይ! የጌታን ቃል ስማ፤ ጌታ ስለ አንተ እንዲህ ይላል፦ ‘በሰይፍ አትሞትም፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ ‘ነገር ግን፣ የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ ሆይ፤ የእግዚአብሔርን ቃል ስማ፤ እግዚአብሔር ስለ አንተ እንዲህ ይላል፤ በሰይፍ አትሞትም፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሴዴቅያስ ሆይ፥ እኔ ስለ አንተ የምለውን ስማ፤ በጦርነት ላይ አትሞትም፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

“ነገር ግን የይ​ሁዳ ንጉሥ ሴዴ​ቅ​ያስ ሆይ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስማ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ አንተ እን​ዲህ ይላል፦ በሰ​ይፍ አት​ሞ​ትም፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ነገር ግን፥ የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስማ፥ እግዚአብሔር ስለ አንተ እንዲህ ይላል፦ በሰይፍ አትሞትም፥ በሰላም ትሞታለህ እንጂ፥

Ver Capítulo



ኤርምያስ 34:4
7 Referencias Cruzadas  

ሚክያስም እንዲህ አለ፦ “እንግዲህ የጌታን ቃል ስሙ፤ ጌታ በዙፋኑ ተቀምጦ፥ የሰማይም ሠራዊት ሁሉ በቀኙና በግራው ቆመው አየሁ።


የያዕቆብ ቤት የእስራኤልም ቤት ወገኖች ሁሉ ሆይ! የጌታን ቃል ስሙ።


እርሱም ሴዴቅያስን ወደ ባቢሎን ያፈልሰዋል፥ እኔም እስክጐበኘው ድረስ በዚያ ይኖራል፥ ይላል ጌታ፤ ከከላዳውያን ጋር ብትዋጉ ምንም አይቀናችሁም’?”


አንተም በእርግጥ ትያዛለህ ለእጁም ተላልፈህ ትሰጣለህ እንጂ ከእጁ አታመልጥም፤ ዓይንህም የባቢሎንን ንጉሥ ዐይን ታያለች፥ እርሱም ከአንተ ጋር ፊት ለፊት ይነጋገራል፥ ወደ ባቢሎንም ትሄዳለህ።’


በሰላም ትሞታለህ። ከአንተ በፊት እንደ ነበሩ እንደ ዱሮ ነገሥታት እንደ አባቶችህ ዕጣን እንደታጠነላቸው፥ እንዲሁ ለአንተም ዕጣንን ያጥኑልሃል፦ “ወየው! ጌታ ሆይ!” እያሉ ያለቅሱልሃል፤’ እኔ ቃልን ተናግሬአለሁና፥ ይላል ጌታ።”


“በጌታ ቤት በር ቁም፥ ይህንም ቃል በዚያ እንዲህ ብለህ አውጅ፦ ጌታን ልታመልኩ በእነዚህ በሮች የምትገቡ የይሁዳ ሰዎች ሆይ! ሁላችሁ የጌታን ቃል ስሙ።


እናንተ የእስራኤል ልጆች ሆይ! እውነትና ጽኑ ፍቅር አምላክንም ማወቅ በምድሪቱ ስለ ሌለ ጌታ በምድሪቱ ላይ ከሚኖሩ ጋር ሙግት አለውና የጌታን ቃል ስሙ።