በግብጽም አማልክት ቤቶች እሳትን አነድዳለሁ፤ የባቢሎንም ንጉሥ ያቃጥላቸዋል ይማርካቸዋልም፤ እረኛም ደበሎውን እንደሚደርብ እንዲሁ የግብጽን አገር ይደርባል፤ ከዚያም ስፍራ በሰላም ይወጣል።
ኤርምያስ 25:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የግብጽንም ንጉሥ ፈርዖንን ባርያዎቹንም አለቆቹንም ሕዝቡንም ሁሉ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የግብጽን ንጉሥ ፈርዖንን፣ አገልጋዮቹን፣ ባለሥልጣኖቹንና ሕዝቡን ሁሉ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከጽዋው መጠጣት የሚገባቸው ሌሎች ደግሞ የሚከተሉት ናቸው፦ የግብጽ ንጉሥ ከባለሟሎቹና ከመኳንንቱ ሁሉ ጋር፥ የግብጽ ሕዝብና በግብጽ የሚኖሩ መጻተኞች ሁሉ፥ በዑፅ ምድር የሚኖሩ ነገሥታት ሁሉ፥ በፍልስጥኤማውያን ከተሞች፥ በአስቀሎና፥ በጋዛ፥ በዔቅሮንና በአሽዶድ፥ በሌሎች ቦታዎችም የሚኖሩ የኤዶም፥ የሞአብና የዐሞን ሕዝቦች ሁሉ፥ የጢሮስና የሲዶና ነገሥታት ሁሉ፥ በሜዲትራኒያን ባሕር ዙሪያ በሚገኙ አገሮች ያሉ ነገሥታት ሁሉ፥ የደዳን፥ የቴማና የቡዝ ከተሞች ሁሉ፥ የግንባራቸውን ግራና ቀኝ ጠጒር የሚላጩ ሕዝቦች ሁሉ፥ የዐረብ አገር ነገሥታት ሁሉ፥ በበረሓ የሚኖሩ ነገዶች ነገሥታት ሁሉ፥ የዘምሪ፥ የዔላምና የሜዶን ነገሥታት ሁሉ፥ ሌሎችም በስተሰሜን በኩል በሩቅና በቅርብ ያሉ ነገሥታት ሁሉ በየተራቸው። በምድር ላይ የሚኖሩት ሕዝብ ሁሉ፥ ከዚህ ጽዋ ይጠጣሉ፤ በመጨረሻም የባቢሎን ንጉሥ ከዚህ ጽዋ መጠጣት ይኖርበታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የግብፅንም ንጉሥ ፈርዖንን፥ አገልጋዮቹንም፥ መሳፍንቱንና መኳንንቱን፤ ሕዝቡንም ሁሉ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የግብጽንም ንጉሥ ፈርዖንን ባሪያዎቹንም አለቆቹንም ሕዝቡንም ሁሉ፥ |
በግብጽም አማልክት ቤቶች እሳትን አነድዳለሁ፤ የባቢሎንም ንጉሥ ያቃጥላቸዋል ይማርካቸዋልም፤ እረኛም ደበሎውን እንደሚደርብ እንዲሁ የግብጽን አገር ይደርባል፤ ከዚያም ስፍራ በሰላም ይወጣል።
ስለ ግብጽ፤ በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ በከርከሚሽ ስለ ነበረው፥ በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም በአራተኛው ዓመት የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ስለ መታው ስለ ግብጽ ንጉሥ ስለ ፈርዖን ኒካዑ ሠራዊት።