ከዚያም ዳዊት ኦርዮን፥ “እንግዲያውስ ዛሬ እዚህ እደርና ነገ አሰናብትሃለሁ” አለው። ስለዚህ ኦርዮ በዚያ ዕለትና በማግስቱ በኢየሩሳሌም ቆየ።
ኤርምያስ 2:37 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያ ደግሞ እጆችሽን በራስሽ ላይ አድርገሽ ትወጫለሽ፥ ምክንያቱም ጌታ የታመንሽባቸውን ጥሎአልና፥ በእነርሱም አይከናወንልሽም።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የታመንሽባቸውን እግዚአብሔር ስላዋረደ፣ በእነርሱም ስለማይከናወንልሽ፣ እጆችሽን በራስሽ ላይ አድርገሽ ከዚያም ትወጫለሽ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እጅሽን በራስሽ ላይ አድርገሽ በዕፍረት ከዚያ ቦታ ትሄጂአለሽ፤ እኔ እግዚአብሔር አንቺ የምትታመኝባቸውን ሁሉ ስላስወገድኩ ከእነርሱ የምታገኚው ምንም ነገር አይኖርም።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ተስፋሽን አስቈርጦሻልና፥ በእርሱም አይከናወንልሽምና እጅሽን በራስሽ ላይ አድርገሽ ከዚያ ደግሞ ትወጫለሽ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር የታመንሽባቸውን ጥሎአልና፥ በእነርሱም አይከናወንልሽምና እጅሽን በራስሽ ላይ አድርገሽ ከዚያ ደግሞ ትወጫለሽ። |
ከዚያም ዳዊት ኦርዮን፥ “እንግዲያውስ ዛሬ እዚህ እደርና ነገ አሰናብትሃለሁ” አለው። ስለዚህ ኦርዮ በዚያ ዕለትና በማግስቱ በኢየሩሳሌም ቆየ።
እነሆም፥ ጌታ በእኛ ላይ አለቃ ነው፥ መለከቱንም የሚነፉ ካህናቱ ከእኛ ጋር ናቸው፥ በእናንተም ላይ የጦርነት ማስጠንቀቅያ ድምፅ ያሰማሉ። የእስራኤል ልጆች ሆይ! አይበጃችሁምና ከአባቶቻችሁ አምላክ ከጌታ ጋር አትዋጉ።”
ከእስረኞች ጋር ከመርበትበት፤ ከታረዱትም ጋር ከመጣል በቀር ምንም አይተርፋችሁም። ይህም ሁሉ ሆኖ፤ ቁጣው ገና አልበረደም። እጁም እንደ ተዘረጋ ነው።
ከሞትም ጋር ያደረጋችሁት ቃል ኪዳን ይፈርሳል፥ ከሲኦልም ጋር የተማማላችሁት መሐላ አይጸናም፤ የሚትረፈረፍ መቅሰፍት ባለፈ ጊዜ ትረገጡበታላችሁ።
ታላላቆቻቸውም ብላቴኖቻቸውን ወደ ውኃ ላኩ፤ ወደ ጉድጓድ መጡ ውኃም አላገኙም፥ ዕቃቸውንም ባዶውን ይዘው ተመለሱ፤ አፈሩም ተዋረዱም ራሳቸውንም ተከናነቡ።
ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ከዚህ ሰው ዘር የሚከናወንለት የለም፥ በዳዊትም ዙፋን ላይ የሚቀመጥ በይሁዳም የሚነግሥ ከእንግዲህ ወዲህ አይገኝምና፦ መካን በዘመኑም የማይከናወንለት ሰው ብላችሁ ጻፉ።”
እርሱም ሴዴቅያስን ወደ ባቢሎን ያፈልሰዋል፥ እኔም እስክጐበኘው ድረስ በዚያ ይኖራል፥ ይላል ጌታ፤ ከከላዳውያን ጋር ብትዋጉ ምንም አይቀናችሁም’?”