ኤርምያስ 15:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በምድሪቱም ደጆች ውስጥ በመንሽ አበጥሬአቸዋለሁ፤ የወላድ መካን አድርጌአቸዋለሁ፥ ሕዝቤንም አጥፍቼአለሁ፤ ከመንገዳቸውም አልተመለሱም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአገሪቱ የከተማ ደጆች፣ በመንሽ እበትናቸዋለሁ፤ ከመንገዳቸው አልተመለሱምና፣ ሕዝቤን በሐዘን እመታለሁ፤ ጥፋትም አመጣባቸዋለሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ገለባ በነፋስ እንደሚበተን፥ በምድሪቱ ውስጥ ባሉት ከተሞች ሁሉ በተንኳችሁ፤ ከክፉ ሥራችሁም ካለመመለሳችሁ የተነሣ፥ እናንተን ሕዝቤን አጠፋኋችሁ፤ ልጆቻችሁ ሁሉ እንዲገደሉ አደረግሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕዝቤንም ወደ ዳርቻ ፈጽሜ እበትናቸዋለሁ፤ የወላድ መካን አድርጌአቸዋለሁ፤ ሕዝቤንም ስለ ኀጢአታቸው አጥፍቻቸዋለሁ፤ ከመንገዳቸውም አልተመለሱም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአገርም ደጆች ውስጥ በመንሽ አበጥሬአቸዋለሁ፥ የወላድ መካን አድርጌአቸዋለሁ፥ ሕዝቤንም አጥፍቼአለሁ፥ ከመንገዳቸውም አልተመለሱም። |
ስለዚህ ልጆቻቸውን ለራብ ስጥ፥ ለሰይፍም እጅ አሳልፈህ ስጣቸው፥ ሚስቶቻቸውም የወላድ መካንና መበለቶች ይሁኑ፥ ወንዶቻቸውም በሞት ይጥፉ፥ ጉልማሶቻቸውም በጦርነት ጊዜ በሰይፍ ይመቱ።
አቤቱ! ዓይንህ እውነትን የምትመለከት አይደለችምን? አንተ ቀሥፈሃቸዋል ነገር ግን አላዘኑም፥ ቀጥቅጠሃቸዋልም ነገር ግን ተግሣጽን ለመቀበል እንቢ አሉ፤ ፊታቸውን ከድንጋይ ይልቅ አጠንክረዋል፤ ለመመለስ እንቢ አሉ።
ለእስራኤል ቤት እንዲህ በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ የኃይላችሁ ትምክሕት፥ የዓይናችሁ ምኞት፥ የነፍሳችሁ ናፍቆት የሆነውን መቅደሴን አረክሳለሁ፤ ትታችኋቸው የሄዳችሁ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁ በሰይፍ ይወድቃሉ።
አንተም የሰው ልጅ ሆይ፥ ምሽጋቸውን፥ የክብራቸውን ደስታ፥ የዓይናቸውን ምኞት፥ የነፍሳቸውን ናፍቆት፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን በወሰድሁባቸው ቀን፥
ሰዎችን፥ ሕዝቤን እስራኤልን፥ በእናንተ ላይ አስሄዳቸዋለሁ፤ እነርሱም ይወርሱሻል ርስትም ትሆኛቸዋለሽ፥ ከእንግዲህም ወዲያ ልጅ አልባ አታደርጊአቸውም።
የቀደሙት ነቢያት ለአባቶቻችሁ እንዲህ ብለው ሰብከዋል፦ “የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘ከክፉ መንገዳችሁና ከክፉ ሥራችሁ ተመለሱ፤’” እነርሱ ግን አልሰሙም፤ እኔንም አላደመጡም፤ እንደ እነርሱ አትሁኑ፥ ይላል ጌታ።
ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ ለሌላ ሕዝብ ይሰጣሉ፤ ነገር ግን ምንም ለማድረግ አትችልም፤ ከዛሬ ነገ ይመጣሉ በማለትም ዐይኖችህ ሁልጊዜ እነርሱን በመጠባበቅ ይደክማሉ።