Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሕዝቅኤል 24:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 አንተም የሰው ልጅ ሆይ፥ ምሽጋቸውን፥ የክብራቸውን ደስታ፥ የዓይናቸውን ምኞት፥ የነፍሳቸውን ናፍቆት፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን በወሰድሁባቸው ቀን፥

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 “አንተም የሰው ልጅ ሆይ፤ ኀይላቸውን፣ ደስታቸውንና፣ ክብራቸውን፣ የዐይናቸው ማረፊያና የልባቸው ደስታ የሆኑትን ወንድና ሴት ልጆቻቸውን ጭምር በምወስድባቸው ቀን፣

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “አሁንም የሰው ልጅ ሆይ! ዘወትር ሊያዩትና ሊጐበኙት የሚወዱትን፥ የሚመኩበትንና የሚደሰቱበትን እጅግ ጽኑ የሆነውን ቤተ መቅደስ ከእነርሱ እወስድባቸዋለሁ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውንም እወስዳለሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 “አን​ተም የሰው ልጅ ሆይ! ኀይ​ላ​ቸ​ውን፥ የተ​መ​ኩ​በ​ት​ንም ደስታ፥ የዐ​ይ​ና​ቸ​ው​ንም አም​ሮት፥ የነ​ፍ​ሳ​ቸ​ው​ንም ምኞት፥ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውን በወ​ሰ​ድ​ሁ​ባ​ቸው ቀን፥

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 አንተም የሰው ልጅ ሆይ፥ ኃይላቸውን፥ የተመኩበትንም ደስታ፥ የዓይናቸውን አምሮት፥ የነፍሳቸውንም ምኞት፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን በወሰድሁባቸው ቀን፥

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 24:25
10 Referencias Cruzadas  

ለእስራኤል ቤት እንዲህ በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ የኃይላችሁ ትምክሕት፥ የዓይናችሁ ምኞት፥ የነፍሳችሁ ናፍቆት የሆነውን መቅደሴን አረክሳለሁ፤ ትታችኋቸው የሄዳችሁ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁ በሰይፍ ይወድቃሉ።


የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ እቀጣቸዋለሁ፤ ጉልማሶቻቸው በሰይፍ ይሞታሉ፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውም በራብ ይሞታሉ፤


ከጽዮን፥ ከውበት ሙላቱ እግዚአብሔር ያበራል።


ጌታ ትልቅ ነው፥ በአምላካችን ከተማ በተቀደሰው ተራራ ምስጋናው ብዙ ነው።


የባቢሎንም ንጉሥ የሴዴቅያስን ልጆች ዓይኑ እያየ ገደላቸው፥ እንዲሁም የይሁዳን አለቆች ሁሉ በሪብላ ገደላቸው።


‘የጌታ መቅደስ፥ የጌታ መቅደስ፥ የጌታ መቅደስ ይህ ነው’ እያላችሁ በእነዚህ የሐሰት ቃላት አትታመኑ።


ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ ለሌላ ሕዝብ ይሰጣሉ፤ ነገር ግን ምንም ለማድረግ አትችልም፤ ከዛሬ ነገ ይመጣሉ በማለትም ዐይኖችህ ሁልጊዜ እነርሱን በመጠባበቅ ይደክማሉ።


ዳሌጥ። ቀስቱን እንደ ጠላት ገተረ፥ እንደ አስጨናቂ ቀኝ እጁን አጸና፥ ለዓይንም የሚያምረውን ሁሉ ገደለ፥ በጽዮን ሴት ልጅ ድንኳን መዓቱን እንደ እሳት አፈሰሰ።


ያመለጠው ሰው ከመምጣቱ በፊት በነበረው ምሽት የጌታ እጅ በእኔ ላይ ነበረች፥ በነጋውም ወደ እኔ እስኪመጣ ድረስ አፌን ከፈተ፤ አፌም ተከፈተ ከዚያም በኋላ ዲዳ አልሆንሁም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios