ሁላችን እንደ ርኩስ ሰው ሆነናል፥ ጽድቃችንም ሁሉ እንደ መርገም ጨርቅ ነው፤ ሁላችንም እንደ ቅጠል ረግፈናል፥ በደላችንም እንደ ነፋስ ወስዶናል።
ኤርምያስ 13:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም ወደ ኤፍራጥስ ሄድሁ ቆፈርሁም፥ ከዚያ ከሸሸግሁበትም ስፍራ መታጠቂያውን ወሰድሁ። እነሆም፥ መታጠቂያው ተበላሽቶ ነበር፥ ለምንም አይረባም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔም ወደ ኤፍራጥስ ሄጄ፣ መታጠቂያውን ከሸሸግሁበት ቦታ ቈፍሬ አወጣሁ፤ መታጠቂያውም ተበላሽቶ፣ ከጥቅም ውጭም ሆኖ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔም ሄጄ መታጠቂያውን የደበቅሁበትን ስፍራ አገኘሁ፤ መታጠቂያውንም ባየሁት ጊዜ ተበላሽቶና ከጥቅም ውጪ ሆኖ አገኘሁት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም ወደ ኤፍራጥስ ወንዝ ሄድሁ፤ ቈፈርሁም፤ ከቀበርሁበትም ስፍራ መታጠቂያዪቱን ወሰድሁ። እነሆም መታጠቂያዪቱ ተበላሽታ ነበር፤ ለምንም አልረባችም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም ወደ ኤፍራጥስ ሄድሁ ቆፈርሁም፥ ከሸሸግሁበትም ስፍራ መታጠቂያይቱን ወሰድሁ። እነሆም፥ መታጠቂያይቱ ተበላሽታ ነበር፥ ለምንም አልረባችም። |
ሁላችን እንደ ርኩስ ሰው ሆነናል፥ ጽድቃችንም ሁሉ እንደ መርገም ጨርቅ ነው፤ ሁላችንም እንደ ቅጠል ረግፈናል፥ በደላችንም እንደ ነፋስ ወስዶናል።
ቃሌን ለመስማት እንቢ የሚሉ፥ በልባቸውም እልከኝነት የሚሄዱ፥ ሊያገለግሉአቸውና ሊሰግዱላቸው ሌሎችን አማልክት የሚከተሉ፥ እነዚህ ክፉ ሕዝብ አንዳች እንደማይረባ እንደዚህ መታጠቂያ ይሆናሉ።