La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 10:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ስለ ስብራቴ ወዮልኝ! ቁስሌም የማይሽር ነው፥ እኔ ግን፦ “በእውነት የመከራ ቁስሌ ነው እርሱንም መሸከም ይገባኛል” አልሁ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ስለ ስብራቴ ወዮልኝ፤ ቍስሌም የማይድን ነው፤ ግን ለራሴ እንዲህ አልሁት፤ “ይህ የኔው ሕመም ነው፤ ልሸከመውም ይገባኛል።”

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የኢየሩሳሌም ሕዝብ እየጮሁ እንዲህ ይላሉ፥ “በብርቱ ስለ ቈሰልን ወዮልን! ቊስላችንም የማይፈወስ ነው፤ እኛ ግን ይህን ሁሉ መከራ መታገሥ የምንችል መስሎን ነበር።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ስለ ስብ​ራቴ ወዮ​ልኝ! ቍስ​ሌም ክፉ ነው፤ እኔ ግን፦ በእ​ው​ነት የመ​ከራ ቁስሌ ነው፤ እር​ሱ​ንም መሸ​ከም ይገ​ባ​ኛል አልሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ስለ ስብራቴ ወዮልኝ! ቍስሌም ክፉ ነው፥ እኔ ግን፦ በእውነት የመከራ ቍስሌ ነው እርሱንም መሸከም ይገባኛል አልሁ።

Ver Capítulo



ኤርምያስ 10:19
17 Referencias Cruzadas  

ከመተላለፌ ሁሉ አድነኝ፥ የሞኞች መሳለቂያ አታድርገኝ።


እግዚአብሔርስ ማዘኑን ረሳን? በቁጣውስ ርኅራኄውን ዘጋውን?


ፊቱን ከያዕቆብ ቤት የሸሸገውን ጌታን እጠብቃለሁ፤ እርሱንም ተስፋ አደርጋለሁ።


ይህን ቃል እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘የወገኔ ልጅ ድንግሊቱ በታላቅ ስብራትና ፈጽሞ በማይሽር ቁስል ቆስላለችና ዐይኖቼ ሌሊትና ቀን ሳያቋርጡ እንባ ያፍስሱ።


“ኃጢአታችን ብዙ ነውና፥ በአንተም ላይ ኃጢአትን ሠርተናል፤ ምንም እንኳ ኃጢአታችን ቢመሰክርብንም ስለ ስምህ ብለህ አቤቱ! አድርግ።


የእስራኤል ተስፋ አቤቱ! የሚተዉህ ሁሉ ያፍራሉ፤ ከአንተም የሚለዩ የሕይወትን ውኃ ምንጭ ጌታን ትተዋልና በምድር ላይ ይጻፋሉ።


አንጀቴ! አንጀቴ! ልቤ በጣም ታምሞአል፥ በውስጤም ልቤ ታውኮብኛል፤ ነፍሴ ሆይ! የመለከትን ድምፅና የጦርነትን ሁካታ ሰምተሻልና ዝም ማለት አልችልም።


እንደታመመች የበኩርዋንም እንደምትወልድ ሴት የጭንቀት ድምፅ ሰምቻለሁና፤ የጽዮን ሴት ልጅ ድምፅ በድካም ታቃስታለች፥ እጆችዋንም በመዘርጋት፦ “በነፍሰ ገዳዮች ፊት ነፍሴ ዝላለችና ወዮልኝ!” አለች።


በሕዝቤ ሴት ልጅ ስብራት እኔ ተሰብሬአለሁ ጠቁሬአለሁም፤ ፍርሀትም ይዞኛል።


ተወግተው ስለ ሞቱት ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ሰዎች ሌሊትና ቀን እንዳለቅስ ራሴ ውኃ፥ ዓይኔም የእንባ ምንጭ በሆነልኝ!


ቤት። በሌሊት እጅግ ታላቅሳለች፥ እንባዋም በጉንጭዋ ላይ አለ፥ ከውሽሞችዋ ሁሉ የሚያጽናናት የለም፥ ወዳጆችዋ ሁሉ ወነጀሉአት ጠላቶችም ሆኑአት።


ስለ ወገኔ ሴት ልጅ ቅጥቃጤ ዓይኔ የውኃ ፈሳሽ አፈሰሰች።


በእርሱ ላይ ኃጢአት ሠርቻለሁና፥ ጉዳዬን እስኪምዋገትልኝ ድረስ፥ ፍርድን እስኪያደርግልኝ ድረስ የጌታን ቁጣ እታገሣለሁ። ወደ ብርሃን ያወጣኛል፥ ጽድቁንም አያለሁ።