ኤርምያስ 10:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ እንዲህ ይላልና፦ “እነሆ፥ በምድሪቱ የሚኖሩትን እስኪሰማቸው ድረስ በዚህ ጊዜ እወነጭፋቸዋለሁ፥ አስጨንቃቸዋለሁም።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤ “በዚህች ምድር የሚኖሩትን፣ አሁን ወደ ውጪ እወነጭፋቸዋለሁ፤ ጕዳቱ እንዲሰማቸው፣ መከራ አመጣባቸዋለሁ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በዚህ ጊዜ በዚህች አገር የሚኖሩትን ሰዎች አስወጣለሁ፤ እነርሱን አስጨንቄ እንዲማረኩ አደርጋለሁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ እነሆ በምድሪቱ የሚኖሩትን በመከራ አሰናክላቸዋለሁ፤ መቅሠፍትሽም እንዲያገኛቸው አስጨንቃቸዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ እነሆ፥ በምድሪቱ የሚኖሩትን እስኪሰማቸው ድረስ በዚህ ጊዜ እወነጭፋቸዋለሁ፥ አስጨንቃቸውማለሁ። |
ስለዚህ ከዚህች ምድር እናንተና አባቶቻችሁ ወዳላወቃችኋት ምድር እጥላችኋለሁ፤ ምሕረትንም አላደርግላችሁምና በዚያ ሌሎችን አማልክት ቀንና ሌሊት ታገለግላላችሁ።’
በሰዎች ላይ ጭንቀትን አመጣለሁ፤ እንደ ዕውርም ይሄዳሉ፥ በጌታ ላይ ኃጢአትን ሠርተዋልና፤ ደማቸው እንደ ትቢያ ይፈስሳል፥ ሥጋቸውም እንደ ጉድፍ ይጣላል።
ነገር ግን ለአገልጋዮቼ ለነቢያት ያዘዝኳቸው ቃሎቼና ሥርዓቴ በአባቶቻችሁ ላይ አልደረሱምን? ከዚያ እነርሱም ተጸጽተው፦ “የሠራዊት ጌታ በመንገዳችንና በሥራችን መጠን ሊያደርግብን ያሰበውን እንዲሁ አድርጎብናል” በማለት ተቀበሉ።
የምትተማመንባቸውን ታላላቅ የተመሸጉ ቅጥሮች እስኪማረኩ ድረስ በመላው አገርህ ያሉትን ከተሞችህን ሁሉ ይከባል፤ ጌታ እግዚአብሔር በሚሰጥህ ምድር ያሉትን ከተሞች በሙሉ ይወራቸዋል።
ማንም ሰው ሕይወትህን ለማጥፋት ቢያሳድድህ እንኳ፥ የጌታዬ ሕይወት በሕያዋን አንድነት እስራት ውስጥ በአምላክህ በጌታ ዘንድ በሰላም ትጠበቃለች፤ የጠላቶችህን ሕይወት ግን፥ እንደ ወንጭፍ ድንጋይ ይወነጭፋል።