ያዕቆብ 2:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመካከላችሁ አድልዎ ማድረጋችሁ አይደለምን? ደግሞስ በክፉ ሐሳብ የተያዛችሁ ፈራጆች መሆናችሁ አይደለምን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመካከላችሁ አድልዎ ማድረጋችሁ አይደለምን? ደግሞስ በክፉ ሐሳብ የተያዛችሁ ፈራጆች መሆናችሁ አይደለምን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ታዲያ፥ በዚህ ዐይነት በመካከላችሁ ልዩነት እንደምታደርጉና የአድልዎ ፍርድ እንደምትፈርዱ አይታያችሁምን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ክፉ አሳብ ያላቸውም ዳኞች መሆናችሁ አይደለምን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ክፉ አሳብ ያላቸውም ዳኞች መሆናችሁ አይደለምን? |
ስለዚህ መንገዴን ስላልጠበቃችሁ፥ በሕግም ለሰው ፊት እንዳዳላችሁ መጠን፥ እኔ ደግሞ በሕዝብ ሁሉ ፊት የተናቃችሁና የተዋረዳችሁ አድርጌአችኋለሁ።
ከላይ የሆነችው ጥበብ ግን በመጀመሪያ ንጽሕት ናት፤ ቀጥሎም ሰላም ወዳድ፥ ደግ፥ እሺ ባይ፥ ምሕረትና መልካም ፍሬ የሞላባት፥ ጥርጥርና ግብዝነት የሌለባት ናት።
ወንድሞች ሆይ! እርስ በርሳችሁ አትወነጃጀሉ፤ ወንድሙን የሚወነጅልና በወንድሙም ላይ የሚፈርድ በሕግ ላይ ክፉ ይናገራል፤ በሕግም ላይ ይፈርዳል። በሕግ ላይ ብትፈርድ ፈራጅ እንጂ ሕግን ፈጻሚ አይደለህም።