ኢሳይያስ 63:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “መጥመቂያውን ብቻዬን ረግጫለሁ፥ ከአሕዛብም አንድ ሰው ከእኔ ጋር አልነበረም፤ በቁጣዬ ረገጥኋቸው በመዓቴም ቀጠቀጥኋቸው፤ ደማቸውም በልብሴ ላይ ተረጭቶአል፥ ልብሴንም ሁሉ አሳድፌአለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እኔ በመጭመቂያው ወይኑን ብቻዬን ረገጥሁ፤ ከመንግሥታት ማንም ከእኔ ጋራ አልነበረም፤ በቍጣዬ ረገጥኋቸው፤ በመዓቴም ጨፈለቅኋቸው፤ ደማቸው በመጐናጸፊያዬ ላይ ተረጭቷል፤ ልብሴንም በክዬዋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ይመልሳል “እኔ ብቻዬን አሕዛብን ሁሉ እንደ ወይን ረገጥኩ፤ ይህን በማደርግበት ጊዜ ከሕዝቦች ከእኔ ጋር ማንም አልነበረም፤ እኔ በቊጣዬ ረገጥኳቸው፤ በመዓቴም አደቀቅኋቸው፤ ደማቸውም በልብሴ ላይ ተረጨ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መጭመቂያውን ብቻዬን ረግጫለሁ፤ ከአሕዛብም አንድ ሰው ከእኔ ጋር አልነበረም፤ በቍጣዬም ረገጥኋቸው፤ በመዓቴም ወደ መሬት ጣልጥህዋቸው፤ ደማቸውንም በምድር ላይ አፈሰስሁ፤ ልብሴም ሁሉ በደም ታለለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መጥመቂያውን ብቻዬን ረግጫለሁ፥ ከአሕዛብም አንድ ሰው ከእኔ ጋር አልነበረም፥ በቍጣዬ ረገጥኋቸው በመዓቴም ቀጠቀጥኋቸው፥ ደማቸዋም በልብሴ ላይ ተረጭቶአል፥ ልብሴንም ሁሉ አሳድፌአለሁ። |
ኢዩም “ኤልዛቤልን ወደ ታች ወርውሩአት!” አላቸው፤ እነርሱም አንሥተው በወረወሩአት ጊዜ ደምዋ በግንቡና በፈረሶች ላይ ተረጨ፤ ኢዩም በሬሳዋ ላይ ፈረሶቹንና ሠረገላውን ነዳበት፤
ሳምኬት። ጌታ ኃያላኖቼን ሁሉ ከውስጤ አስወገዳቸው፥ ጐልማሶቼን ያደቅቅ ዘንድ ጉባኤን ጠራብኝ፥ ጌታ ድንግሊቱን የይሁዳን ልጅ በመጥመቂያ እንደሚረገጥ አድርጎ ረገጣት።
በአንድ ላይም እንደ ጦረኞች ይሆናሉ፥ ጠላቶቻቸውንም በመንገድ ጭቃ ውስጥ የሚረግጡ ይሆናሉ፤ ጌታም ከእነርሱ ጋር ስለሆነ ጦርነት ይገጥማሉ፥ ፈረሰኞችንም ያሳፍራሉ።