ኢሳይያስ 59:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰውም እንደሌለ አየ፥ ወደ እርሱ የሚማልድ እንደሌለ ተረዳ፤ ስለዚህ የገዛ ክንዱ መድኃኒት አመጣለት፥ የራሱም ጽድቅ ደገፈው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ማንም እንደሌለ አየ፤ ወደ እርሱ የሚማልድ ባለመኖሩ ተገረመ፤ ስለዚህ የገዛ ክንዱ ድነት አመጣለት፤ የራሱም ጽድቅ ደግፎ ያዘው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ተጨቋኞችን የሚረዳ አንድ ሰው እንኳ አለመገኘቱ አስገረመው፤ ስለዚህ እነርሱን ለማዳን በኀይሉ ተጠቅሞ ድልን እንዲጐናጸፉ አደረጋቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰውም እንደሌለ አየ፤ የሚረዳም ሰው እንደሌለ ተረዳ፤ ሰለዚህ በክንዱ ደገፋቸው፤ በይቅርታውም አጸናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰውም እንደ ሌለ አየ፥ ወደ እርሱ የሚማልድ እንደ ሌለ ተረዳ ተደነቀም፥ ሰለዚህ የገዛ ክንዱ መድኃኒት አመጣለት፥ ጽድቁም አገዘው። |
በመጣሁስ ጊዜ ሰው ስለምን አልነበረም? በጠራሁስ ጊዜ የሚመልስ ስለምን አልነበረም? መታደግ እንዳትችል እጄ አጭር ሆናለችን? ወይስ ለማዳን ኃይል የለኝም? እነሆ፥ በገሠጽሁ ጊዜ ባሕርን አደርቃለሁ፥ ወንዞችንም ምድረ በዳ አደርጋቸዋለሁ፤ ውኃም አጥተው ዓሦቻቸው ይገማሉ፥ በጥማትም ይሞታሉ።
የጌታ ክንድ ሆይ! ተነሥ፥ ተነሥ፥ ኃይልንም ልበስ፤ በቀድሞው ወራትና በጥንቱ ዘመን በነበረው ትውልድ እንደ ሆነው ተነሥ። ረዓብን የቈራረጥህ ዘንዶውንም የወጋህ አንተ አይደለህምን?
በኢየሩሳሌም መንገድ እየተመላለሳችሁ ሩጡ፥ ተመልከቱም፥ እወቁም፥ በአደባባይዋም ፈልጉ፤ ፍርድን የሚያደርገውን እውነትንም የሚሻውን ሰው ታገኙ እንደሆነ ይቅር እላታለሁ።