ኢሳይያስ 57:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ ጽድቅሽን እናገራለሁ፥ ሥራሽም አይረዳሽም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጽድቅሽንና ሥራሽን አጋልጣለሁ፤ እነርሱም አይጠቅሙሽም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ትክክል ናቸው ብላችሁ የምታስቡአቸውን ሥራዎቻችሁን አጋልጣለሁ፤ ጣዖቶቻችሁም ሊረዱአችሁ አይችሉም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዲህ እኔ ጽድቄንና የማይረባሽን የአንቺን በደል እናገራለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ ጽድቅሽን እናገራለሁ፥ ሥራሽም አይረባሽም። |
የተቀረጸውን ምስል የሚሠሩ ከንቱዎች ናቸው፤ የወደዱትም ነገር አይጠቅማቸውም፤ ምስክሮቻቸውም አያስተውሉም ደግሞ አያውቁም፥ ስለዚህ ያፍራሉ።
ጽድቅን የሚያደርገውን፥ በመንገዶችህም የሚያስቡህን ትገናኛቸዋለህ። እኛ ኃጢአት ሠራን፤ እነሆ፥ አንተ ተቈጥተህ ነበር፤ ፊትህን ስለሰወርክብን እኛ ተሳሳትን።
ሰው ሁሉ ቂላ ቂልና እውቀት የሌለው ሆኖአል፥ አንጥረኛም ሁሉ ከቀረጸው ምስል የተነሣ አፍሮአል፤ ቀልጦ የተሠራ ምስሉ ውሸት ነውና፥ እስትንፋስም የላቸውምና።
“እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን! መንግሥተ ሰማያትን በሰዎች ፊት ስለምትዘጉ ወዮላችሁ፤ እናንተ ራሳችሁ አትገቡም፤ የሚገቡትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ።