ኢሳይያስ 49:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተራሮቼንም ሁሉ መንገድ አደርጋለሁ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ተራሮቼን ሁሉ መንገድ አደርጋለሁ፤ ጐዳናዎቼም ከፍ ይላሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ተራሮቼን ደልድዬ መንገድ አደርጋለሁ፤ ጐዳናዎቼም ከፍ ይላሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተራሮችንም ሁሉ መንገድ አደርጋለሁ፤ ጎዳናዎችም ሁሉ መሰማርያ ይሆናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ተራሮቼንም ሁሉ መንገድ አደርጋለሁ፥ |
በዚያ ቀን ከግብጽ ወደ አሦር መንገድ ይዘረጋል፤ አሦራዊያንም ወደ ግብጽ፥ ግብፃዊውም ወደ አሦር ይሄዳሉ፤ ግብፃውያንም ከአሦራውያን ጋር ይሰግዳሉ።
እነሆ፥ አዲስ ነገርን አደርጋለሁ፤ እርሱም አሁን ይበቅላል፥ ይህን እናንተም አታውቁም? በምድረ በዳም መንገድን በበረሃም ወንዞችን እዘረጋለሁ።