ኢሳይያስ 46:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህን አስቡና አልቅሱ፤ ተላላፊዎች ሆይ፥ ንስሐ ግቡ፥ ልባችሁንም መልሱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እናንተ በደለኞች፣ ይህን አስታውሱ፤ አስቡበትም፤ በልባችሁም ያዙት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እናንተ ዐመፀኞች! በአእምሮአችሁ ያዙት፤ በልባችሁም አኑሩት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህን ዐስቡና አልቅሱ፤ የተሳሳታችሁ ሆይ፥ ንስሓ ግቡ፤ ልባችሁንም መልሱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህን አስቡና አልቅሱ፥ ተላላፊዎች ሆይ፥ ንስሐ ግቡ፥ ልባችሁንም መልሱ። |
አልሰማህም፥ አላወቅህም፥ ጆሮህ ከጥንት አልተከፈተችም፤ አንተ ፈጽሞ ወንጀለኛ እንደሆንህ ከማኅፀንም ጀምረህ ተላላፊ ተብለህ እንደ ተጠራህ አውቄአለሁና።
ጌታ እንዲህ ይላል፦ እናታችሁን የፈታሁበት የፍቺዋ ጽሕፈት የት አለ? ወይስ እናንተን የሸጥሁ ከአበዳሪዎች ለየትኛው ነው? እነሆ፥ ስለ ኃጢአታችሁ ተሸጣችኋል፥ ስለ በደላችሁም እናታችሁ ተፈታለች።