La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢሳይያስ 4:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በዚያን ቀን ሰባት ሴቶች አንዱን ወንድ ይዘው፤ “የራሳችንን ምግብ እንበላለን፤ የራሳችንንም ልብስ እንለብሳለን፤ በአንተ ስም ብቻ እንጠራና፤ ውርደታችንን አስቀርልን” ይሉታል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በዚያ ቀን ሰባት ሴቶች አንዱን ወንድ ይዘው፣ “የራሳችንን ምግብ እንበላለን፤ የራሳችንንም ልብስ እንለብሳለን፤ በአንተ ስም ብቻ እንጠራና፣ ውርደታችንን አስቀርልን!” ይሉታል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በዚያን ጊዜ ሰባት ሴቶች አንዱን ወንድ ይዘው “በምግብም ሆነ በልብስ ራሳችንን ችለን እንተዳደራለን፤ ‘ባል የላቸውም’ ተብለን ከመሰደብ እንድንድን የአንተ ሚስቶች ተብለን እንድንጠራ ብቻ ፍቀድልን” ብለው ይለምኑታል።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በዚ​ያም ቀን ሰባት ሴቶች፥ “የገዛ እን​ጀ​ራ​ች​ንን እን​በ​ላ​ለን፤ የገዛ ልብ​ሳ​ች​ን​ንም እን​ለ​ብ​ሳ​ለን፤ ስምህ ብቻ በእኛ ላይ ይጠራ፤ መሰ​ደ​ባ​ች​ን​ንም አር​ቅ​ልን” ብለው አን​ዱን ወንድ ይይ​ዙ​ታል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በዚያም ቀን ሰባት ሴቶች፦ የገዛ እንጀራችንን እንበላለን የገዛ ልብሳችንንም እንለብሳለን፥ ስምህ ብቻ በእኛ ላይ ይጠራ፥ መሰደባችንንም አርቅ ብለው አንዱን ወንድ ይይዙታል።

Ver Capítulo



ኢሳይያስ 4:1
15 Referencias Cruzadas  

ፀነሰችም፥ ወንድ ልጅንም ወለደችና፦ “እግዚአብሔር ስድቤን አስወገደ” አለች፥


የሳኦልም ልጅ ሜልኮል እሰከሞተችበት ጊዜ ድረስ ልጅ አልወለደችም ነበር።


በዚያን ቀን ከእስራኤል ዘር የተረፉት፤ ከያዕቆብም ቤት የዳኑት፤ ከእንግዲህ ወዲህ በመታቸው ላይ አይታመኑም፤ ነገር ግን በእስራኤል ቅዱስ በጌታ ላይ፤ በእውነት ይታመናሉ።


ሰውን ከነጠረ ወርቅ ይልቅ ውድ፤ ከኦፊርም ወርቅ ይበልጥ ብርቅ አደርጋለሁ።


በዚያ ቀን ሰዎች ወደ ፈጣሪያቸው ይመለከታሉ፤ ዐይኖቻቸውም ወደ እስራኤል ቅዱስ ያያሉ።


የእብሪተኛ ሰው ዐይን ይሰበራል፤ የሰዎችም ትዕቢት ይዋረዳል፤ በዚያን ቀን ጌታ ብቻውን ከፍ ከፍ ይላል።


የሰው እብሪት ይዋረዳል፤ የሰውም ኩራት ይወድቃል፤ በዚያን ቀን ጌታ ብቻ ከፍ ከፍ ይላል፤


ሰውም በአባቱ ቤት ከወንድሞቹ አንዱን ይዞ፤ “አንተ ልብስ ስላለህ መሪ ሁነን፤ ይህንንም የፍርስራሽ ክምር ግዛ” ይለዋል።


አታፍሪምና አትፍሪ፤ አትዋረጂምና አትደንግጪ፤ የሕፃንነትሽንም እፍረት ትረሺዋለሽ፥ የመበለትነትሽንም ስድብ ከእንግዲህ ወዲህ አታስቢም።


መበለቶቻቸውም ከባሕር አሸዋ ይልቅ በዝተውብኛል፤ በብላቴኖች እናት ላይ በቀትር ጊዜ አጥፊውን አምጥቻለሁ፤ ጣርንና ድንጋጤን በድንገት አምጥቼባታለሁ።


“ጌታ እኔን በተመለከተበት ጊዜ ነቀፌታዬን ከሰው መካከል አስወገደልኝ።”


የተጻፈው ሁሉ እንዲፈጸም ይህ የቅጣት ጊዜ ነውና።


እንደነዚህ ያሉትንም ሥራቸውን በጸጥታ እየሠሩ የገዛ እንጀራቸውን እንዲበሉ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እናዛቸዋለን፤ እንመክራቸዋለንም።


ጌታ ማሕፀኗን ስለዘጋም ጣውንቷ ሆን ብላ ታስቆጣት፥ ታበሳጫትም ነበር።