Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ተሰሎንቄ 3:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 እንደነዚህ ያሉትንም ሥራቸውን በጸጥታ እየሠሩ የገዛ እንጀራቸውን እንዲበሉ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እናዛቸዋለን፤ እንመክራቸዋለንም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 እንደዚህ ያሉ ሰዎች ተግተው ሥራቸውን እንዲሠሩና እንጀራቸውን እንዲበሉ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዝዛቸዋለን፤ እንመክራቸዋለንም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 እንደእነዚህ ያሉ ሰዎች ተረጋግተው እንዲሠሩና መተዳደሪያቸውን እንዲያገኙ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዛቸዋለን፤ እንመክራቸዋለንም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 እንደነዚህ ያሉትንም በጸጥታ እየሠሩ የገዛ እንጀራቸውን ይበሉ ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እናዛቸዋለን፤ እንመክራቸውማለን።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 እንደነዚህ ያሉትንም በጸጥታ እየሠሩ የገዛ እንጀራቸውን ይበሉ ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እናዛቸዋለን እንመክራቸውማለን።

Ver Capítulo Copiar




2 ተሰሎንቄ 3:12
9 Referencias Cruzadas  

በጸጥታ ለመኖር እንድትተጉ፥ በራሳችሁም ጉዳይ ላይ እንድታተኩሩ፥ እንዳዘዝናችሁም በራሳችሁ እጅ እንድትሰሩ እንለምናችኋለን፤


የሰረቀ ከእንግዲህ ወዲህ አይስረቅ፤ ነገር ግን በዚያ ፈንታ ለጎደለው የሚያካፍለው እንዲኖረው በገዛ እጆቹ መልካምን እየሠራ ይድከም።


ከእናንተ ዘንድ በማንም ላይ ሸክም እንዳንሆንበት ሌሊትና ቀን በድካምና በጥረት እየሠራን እንኖር ነበር እንጂ የማንንም ሰው እንጀራ እንዲያው በነፃ አልበላንም።


እንግዲህ በቀረውስ ወንድሞች ሆይ! እግዚአብሔርን ለማስደሰት እንዴት መመላለስ እንደሚገባችሁ ከእኛ ዘንድ ተቀብላችኋል፤ በእርግጥም እየተመላለሳችሁ ነው፤ ከዚህም በበለጠ አብዝታችሁ እንድታደርጉት በጌታ በኢየሱስ እንለምናችኋለን፤ እንመክራችኋለንም።


የዕለት እንጀራችንን ዕለት ዕለት ስጠን፤


በድካምና ነፋስን በመከተል ከሚገኝ ሁለት እፍኝ ይልቅ፥ በእርጋታ የሚገኝ አንድ እፍኝ ይሻላል።


ጥል ባለበት ዘንድ ግብዣ ከሞላበት ቤት ይልቅ በጸጥታ ደረቅ ቁራሽ ይሻላል።


እንዲሁም እግዚአብሔርን በመምሰልና በተገባ አካሄድ ሁሉ፥ ጸጥታ የሰፈነበትና ሰላማዊ የሆነ ሕይወት እንዲኖረን ስለ ነገሥታትና በከፍተኛ ሥልጣን ላይ ስላሉ ሁሉ ጸሎት እናቅርብ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios