ኢሳይያስ 38:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ጌታ ሆይ፥ በዚህ ነገር ሰዎች በሕይወት ይኖራሉ፥ በዚህም ሁሉ የመንፈሴ ሕይወት ነው፤ አንተም ፈወስከኝ ወደ ሕይወትም መለስከኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጌታ ሆይ፤ ሰዎች በእነዚህ ነገሮች ይኖራሉ፤ መንፈሴም እንዲሁ በእነዚህ ሕይወትን ያገኛል፤ ፈወስኸኝ፤ በሕይወትም አኖርኸኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነፍሴ ካንተ ሕይወትን ታገኛለች፤ ለመንፈሴ ዕረፍትን ስጣት፤ ጤንነቴን እንደ ነበረ አድርግልኝ፥ ሕይወትንም ስጠኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታ ሆይ፥ ስለ እርስዋ እንዲህ አልሁህ፤ ነፍሴን አዳንሃት፤ ደስ አለኝ፤ በሕይወትም ኖርሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጌታ ሆይ፥ በዚህ ነገር ሰዎች በሕይወት ይኖራሉ፥ በዚህም ሁሉ የመንፈሴ ሕይወት ነው፥ አንተም ፈወስኸኝ ወደ ሕይወትም መለስኸኝ። |
ጽድቅን የሚያደርገውን፥ በመንገዶችህም የሚያስቡህን ትገናኛቸዋለህ። እኛ ኃጢአት ሠራን፤ እነሆ፥ አንተ ተቈጥተህ ነበር፤ ፊትህን ስለሰወርክብን እኛ ተሳሳትን።
ሰው የሚኖረው በእንጀራ ብቻ ሳይሆን ከጌታ አፍ በሚወጣ ነገር ሁሉ በሕይወት እንዲኖር ሊያሳውቅህ አስጨነቀህ፥ አስራበህም፥ አንተም ያላወቅኸውን፥ አባቶችህም ያላወቁትን መና አበላህ።
ከዚህም በተጨማሪ የቀጡን የሥጋችን አባቶች ነበሩን፤ እናከብራቸውም ነበር፤ ታዲያ እንዴት በላቀ ለመናፍስት አባት አብልጠን ልንገዛና በሕይወት ልንኖር አይገባንም?