ኢሳይያስ 36:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በንጉሡ በሕዝቅያስ በዓሥራ አራተኛው ዓመት፥ የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም ወደ ተመሸጉት ወደ ይሁዳ ከተሞች ሁሉ ወረራ በመፈጸም ያዛቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሥ ሕዝቅያስ በነገሠ በዐሥራ አራተኛው ዓመት፣ የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም የተመሸጉትን የይሁዳ ከተሞች ሁሉ አጥቅቶ ያዛቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቅያስ በይሁዳ በነገሠ በዐሥራ አራተኛው ዓመት፥ የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም በተመሸጉት የይሁዳ ከተሞች ላይ አደጋ ጥሎ ያዛቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም ሆነ፤ በንጉሡ በሕዝቅያስ በዐሥራ አራተኛው ዓመተ መንግሥት የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም ወደ ይሁዳ ወደ ተመሸጉት ከተሞች ሁሉ ወጥቶ ወሰዳቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም ሆነ፥ በንጉሡ በሕዝቅያስ በአሥራ አራተኛው ዓመት የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም ወደ ይሁዳ ወደ ተመሸጉት ከተሞች ሁሉ ወጥቶ ወሰዳቸው። |
ይህ በዚህ እንዳለ የአሦር ንጉሠ ነገሥት እንደገና የተጠናከረ ታላቅ ሠራዊት ከላኪሽ ተንቀሳቅሶ ወደ ኢየሩሳሌም በመዝመት በሕዝቅያስ ላይ አደጋ እንዲጥልበት አዘዘ፤ ያም ሠራዊት ከፍተኛ ሥልጣን ባላቸው ሦስት የጦር አዛዦቹ የሚመራ ነበር፤ እነርሱም ወደ ኢየሩሳሌም እንደ ደረሱ ከላይኛው ኲሬ ውሃ በሚተላለፍበት ቦይ አጠገብ ወደ ልብስ አጣቢዎች መስክ የሚወስደውን መንገድ ያዙ፤
ከዚህም ነገርና በታማኝነት ከተደረገው ነገር በኋላ የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም መጥቶ ወደ ይሁዳ ገባ፥ በተመሸጉትም ከተሞች ፊት ሰፈረ፥ የራሱም ሊያደርጋቸው አሰበ።
ኤፍሬም ከይሁዳ ከተለየበት ቀን ጀምሮ ታይቶ የማይታወቅ ዘመን በአንተ፤ በሕዝብህና በአባትህ ቤት ላይ ያመጣል፤ የሚያመጣውም የአሦርን ንጉሥ ነው።