ኢሳይያስ 34:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የምድረ በዳም አራዊት ከጅቦች ጋር ይገናኛሉ፤ አጋንንትም እርስ በርሳቸው ይጠራራሉ፤ ጅንም በዚያም ትኖራለች፤ ለእርሷም ማረፊያ ታገኛለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የምድረ በዳ አራዊት ከጅቦች ጋራ ዐብረው ይሆናሉ፤ በበረሓ ፍየል የሚመሰሉ አጋንንትም እርስ በእርስ ይጠራራሉ፤ የሌሊት ፍጥረታት ማረፊያቸውን በዚያ ያደርጋሉ፤ ለራሳቸውም የማረፊያ ቦታ ያገኛሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አነሮች ከጅቦች ጋር አብረው ይኖራሉ፤ አጋንንትም እርስ በርሳቸው ይጠራራሉ፤ የሌሊት ምትሐቶች በፍርስራሾች መካከል ይኖራሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም አጋንንትና ጂኖች ይገናኛሉ፤ እነርሱም እርስ በርሳቸው ይጠራራሉ፤ ጂኖችም በዚያ ይኖራሉ፤ ለራሳቸውም ማረፊያን ያገኛሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የምድረ በዳም አራዊት ከተኵሎች ጋር ይገናኛሉ፥ አጋንንትም እርስ በርሳቸው ይጠራራሉ፥ ጅንም በዚያም ትኖራለች፥ ለእርስዋም ማረፊያ ታገኛለች። |
ስለዚህ በባቢሎን የምድረ በዳ አራዊት ከተኩላዎች ጋር ይቀመጡባታል፥ ሰጐኖችም ይቀመጡባታል፤ ሰውም ከዚያ ወዲያ ለዘለዓለም አይቀመጥባትም፥ እስከ ልጅ ልጅም ድረስ የሚኖርባት የለም።