ኢሳይያስ 34:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 በዚያም ጉጉት ጎጆ ሠርታ እንቁላልን ትጥላለች፥ ትቀፈቅፋለችም፤ ጫጩቶቿንም በክንፏ ትሰበስባለች፤ በዚያም ደግሞ አሞራዎች ጥንድ ጥንድ ሆነው ይሰበሰባሉ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም15 ጕጕት በዚያ ጐጆ ሠርታ ዕንቍላል ትጥላለች፤ ትቀፈቅፋለች፤ ጫጩቶቿን በክንፎቿ ትታቀፋቸዋለች፤ ጭላቶችም ጥንድ ጥንድ ሆነው፣ ለርቢ በዚያ ይሰበሰባሉ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም15 በዚያም ጒጒቶች ጎጆ ሠርተው እንቊላል ይጥላሉ፤ እንቁላሎቻቸውንም ፈልፍለው በክንፎቻቸው ጥላ ሥር ይንከባከባሉ፤ አሞራዎችም ከጓደኞቻቸው ጋር በዚያ ይሰባሰባሉ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 በዚያ ጃርቶች ይዋለዳሉ፤ ምድርም ልጆችዋን በኀይል ታድናለች፤ ዋሊያዎች በዚያ ይገናኛሉ፤ ፊት ለፊትም ይተያያሉ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)15 በዚያም ዋሊያ ቤትዋን ትሠራለች እንቍላልን ትጥላለች ትቀፈቅፈውማለች ልጆችዋንም በጥላዋ ትሰበስባለች፥ በዚያም ደግሞ አሞራዎች እያንዳንዳቸው ከባልንጀሮቻቸው ጋር ይሰበሰባሉ። Ver Capítulo |